ዓለም አቀፍ ደረጃ ስለ ኤድስ ግንዛቤ የሚሰጥበት ቀን
ዓርብ፣ ኅዳር 21 2016
ማስታወቂያ
ዓለም አቀፍ ደረጃ ስለ ኤድስ ግንዛቤ የሚሰጥበት ቀን
በዓለም አቀፍ ደረጃ የኤድስ ተዉሳክን ለማጥፋት የሚደረገዉ ምርምር እንደቀጠለ ቢሆንም እንስካሁን ክትባትም ሆነ ተዉሳኩን ከሰዉነት ማጥፍያ መድሐኒት አለመገኘቱ ተገለፀ ። ይሁንና ዉጤታማ የሆኑ መድሐኒቶች በመኖራቸዉ የብዙዎችን ህይወት መታደግ መቻሉ ተዘግቧል። ይህ ይፋ የሆነዉ ዛሬ የተባበሩት መንግሥታት በደነገገዉ መሰረት በዓለም አቀፍ ደረጃ ዛሬ ስለኤድስ ግንዛቤ የሚሰጥበት እና የሚታወስበትን እለት ተከትሎ ነዉ። የኤድስ ቫይረስን ለማዳከም እና በተዉሳኩ የተያዙ ሰዎች ቫይረሱ ሰዉነታቸዉን እንዳይጎዳ የሚያደርግ በእጅጉ የተሻሻለ መድሐኒት አይነት በመኖሩ ዉጤታማ መሆኑ ተመልክቷል። በአሁኑ ወቅት በኤድስ ቫይረስ የተጠቁ ሰዎች በቀን አንድ ወይም ሁለት ፍሪ ኪኒን ብቻ በመዉሰድ የኤድስ ቫይረስ ሰዉነታቸዉን እንዳይጎዳ በደማቸዉ የሚገኘዉ የኤድስ ተዉሳክ መጠን እንዲቀንስ ማድረግ ተችሏል ተብሏል። በኤድስ የተያዘ ሰዉ በየሦስት ወሩ ምርመራን በማካሄድ ሰዉነት ዉስጥ ያለዉ የኤድስ ተዉሳክ መጠንን መቀነስ መጨመሩን ማወቁ አስፈላጊ እንደሆንም ተመልክቷል።
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ