ዓለም አቀፍ የዕውቀት ልውውጥ
ረቡዕ፣ ነሐሴ 1 2005የሚይዙት : በየዘርፉ የተሠማሩ ተማራማሪ ምሁራን ናቸው። በእንዲህ ሁኔታ የሚስፋፋውን ዕውቀት፣ በተመክሮ ከዳበረ ዕውቀትና ልምድ ጋር አጣምሮ መጠቀሙ ፣ ለታዳጊ ሀገራት በተለይ ፣ አብነቱ የሚያጠያይቅ አይደለም።
ጥቂት ኢትዮጵያውያን ምሁራን ፣ በብሪታንያ መዲና ፣ በለንደን ፣ የጀመሩት ተሰባስቦ የመምከር፤ ሐሳብ የመለዋወጥ ተመክሮ ፣ ሰፊ ጠቀሜታ እንዳለው ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሥመሰከረ ሳይመጣ አልቀረም።
ዘመኑ ባስገኘው የኢንተርኔት መገናኛ ስልት የሚመክሩ ኢትዮጵያውያን ምሁራን ፣ በዚሁ የግንኙነት መረብ ብቻ ሳይሆን በአካልም ፤ ከዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ወዳጅ ምሁራን ጋር እየተገናኙ የሚመክሩበት መድረክ ዘንድሮም ሆነ በመጪው ዓመት በኅዳር ወር 2ኛ ሳምንት ገደማ ላይ 3ዓመት ይሆነዋል።
ለመጪው ጉባዔ፣ ተመራማሪዎች በአጠቃላይ ምሁራን ጠቃሚ ጽሑፎቻቸውን እስከ ነሐሴ 9 ,2005 (እ ጎ አ እስከ ነሐሴ 15 ,2013)እንዲያቀርቡ ተጠይቀዋል። የዚህ ዓይነቱ ጉባዔ ፣ ለሀገር ዕድገት ካለው አስተዋጽዖ አኳያ፣ የጉባዔውን ዋና አስተባባሪና ሊቀመንበር ፤ የ London South Bank University ባልደረባ የሆኑትን ዶክተር አማረ ደስታን ለቀጣዩ ጉባዔ የምርምር ውጤቶች እንዲቀርቡ ለተላላፈው ጥሪ እስካሁን ምን ዓይነት ምላሽ እንደተገኘ ያብራሩልን ዘንድ ጠይቄአቸው ነበር---------
(ድምፅ)
ተክሌ የኋላ
ሸዋዬ ለገሰ