1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ዓመት በዓልን ከስደት መልስ ሀገር ላይ ማክበር ስንቶች የሚያገኙት ዕድል ይሆን?

ሰለሞን ሙጬ
ሐሙስ፣ መስከረም 1 2018

በሕጋዊም፣ በሕገ - ወጥም መንገድ ወደ መካከለኛው ምስራቅ የአረብ ሀገራት ኑሮን ለማሻሻል ገንዘባቸውን አውጥተው ተጉዘው፣ ለዓመታት በስቃይ የሚቆዩ ሰዎች በዚያ እያሉ ዓመት በዓልን ማክበር የቅንጦት ያህል የሚቆጥሩት ጉዳይ ነው። ዕድሉን አያገኙምና። ገነት ቢቂላ እና ታደለች ታደሰ ከዓመታት የቤይሩት አስቸጋሪ የሥራ ቆይታ በኋላ የተመለሱ ናቸው።

ሳጅን ገነት ቢቂላ
ሳጅን ገነት ቢቂላምስል፦ Solomon Muchie/DW

ዓመት በዓልን ከስደት መልስ ሀገር ላይ ማክበር ስንቶች የሚያገኙት ዕድል ይሆን?

This browser does not support the audio element.

ዓመት በዓልን ከስደት መልስ ሀገር ላይ ማክበር ስንቶች የሚያገኙት ዕድል ይሆን? 

በሕጋዊም፣ በሕገ - ወጥም መንገድ ወደ መካከለኛው ምስራቅ የአረብ ሀገራት ኑሮን ለማሻሻል ገንዘባቸውን አውጥተው ተጉዘው፣ ለዓመታት በስቃይ የሚቆዩ ሰዎች በዚያ እያሉ ዓመት በዓልን ማክበር የቅንጦት ያህል የሚቆጥሩት ጉዳይ ነው። ዕድሉን አያገኙምና። ገነት ቢቂላ እና ታደለች ታደሰ ከዓመታት የቤይሩት አስቸጋሪ የሥራ ቆይታ በኋላ ወደ ሀገራቸው የመመለስ ዕድል ካገኙ ሰዎች መካከል ናቸው። እነዚህ ሴቶች አሁን የየራሳቸው ሥራ ላይ ተሰማርተዋል። እስራኤል በሊባኖስ የከፈተችው ጦርነትና የኢራን የሚሳይል ጥቃት ወዴት ያመራ ይሆን?

እነሱን ጨምሮ ሌሎች ከስደት የሚመለሱ ኢትዮጵያውያንን ተቀብሎ ከሚያስጠልል፣ የሥነ ልቦናም፣ የገንዘብም ድጋፍ ከሚያደርግ ድርጅት ማዕከል ውስጥ እዚያ ስደት ላይ እያሉ ያላገኙትን የ2018 ዓ.ም አዲስ ዓመት ክብረ በዓል በሀገር ባሕል ወግ በጋራ ሲያከብሩ ደስታቸው በስደት ያለፉትን ፈተና ለመርሳት እንዳገዛቸው አጫውተውናል። ስደት በተለይም ሕገ - ወጡ አማራጭ በርካቶችን በበረሃ እየገረፈ፣ በሀይቅና ውቅያኖስ፣ በጫካም እያስቀረ ያለ ተስፋ ቀባሪ ማህበራዊ ችግነቱ ቀጥሏል። ከአውሬ ያመለጡት በደላላ እና አዘዋዋሪዎች በረሃብ፣ በውኃ ጥም ፣ በጉልበት ብዝበዛ እንዲቀጡም ያደርጋል። 

ሳጅን ገነት ቢቂላ 2010 ዓ.ም መግቢያ ላይ ነበር ወደ ሊባኖስ በአውሮፕላን ተሳፍራ ያመራችው። ለሦስት ዓመት ከሦስት ወር በዚያ በተለያየ ሁኔታ ቆይታለች። በቤይሩት የምትኖር ጓደኛዋ ግፊት አድርጋ ነበር ለተሻለ ሥራ በሚል የፖሊስነት ሥራዋን ትታ  የሄደችው።  በሊባኖስ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሁኔታ

"ልጅነትህን ይቀማሃል [ስደት] ካላወቅክበት። ካልተጠቀምክበት።" 

የሠሩበትን መከልከል፣ እያዛለሁ በሚል የሥጋት ሕይወት መግፋት፣ ከዓመታት በፊት ሊባኖስ ወደብ ላይ የተፈጠረው ፍንዳታ ያስከተለው ቀውስ፣ የሥራ ክፍያ ከቤት ክራይ እና ከምግብ የዘለለ አለመሆን በወቅቱ መሄዷን እንድትወቅስ አድርጓታል። ታደለች ታደሰ በሁለት የተለያየ ወቅት ወደ ቤይሩት ተጉዛለች። አንዱን በሕጋዊ መንገድ፣ ሌላኛውን ሕጋዊ በሚመስል ሕገ ወጥ መንገድ። 13 ዓመት በዚያ በሥራ ቆይታለች። ፈተናው ግን ብዙ ነበር። 

የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት አከባበር 2018 ምስል፦ Solomon Muchie/DW

"የሄድኩበት ዋናው ዓላማየ ልጆቼን ለማስተማር ነበር። እንዳሰብኩት አልሆነም።" 

እነዚህ ሁለት ሴቶች በአረብ ሀገር በቤት ሠራተኝነት ሲሠሩ እዚህ የለመዷቸው ክብረ በዓላት እንዲሁ ያልፋሉ እንጂ ዕድሉን አያገኙም። ወደ ሀገራቸው ከተመለሱ በኋላ ግን እነሱን ጨምሮ ሌሎች ተመላሾችን እየተቀበለ ከሚያስጠልለው እና ከሚያግዘው አጋር ኢትዮጵያ ውስጥ በደስታ ማሳለፍ በመቻላቸው ደስተኞች እንደሆኑ ነግረውናል።  ከሊባኖስ የውጭ ሰራተኞችን ለማስወጣት የሚደረገው ጥረት

ስደትን ማን ይመርጣል? ያውም ሕገ ወጡን! ምርጫ ካልጠፋ በቀር። ስደት ሙሉ ለሙሉ ይቆማል ባይባልም ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ግጭቶች፣ ጦርነት፣ ሥራ ማጣት፣ አግላይ አሠራርና መድሎዎች ከገፊ ምክንያቶች የሚጠቀሱ መሆናቸውን ተመላሾች በተለያየ ጊዜ ይጠቅሳሉ። በዚህ ባለፉው ዓመት እንኳን በምያንማር፣ በጅቡቲ፣ በጣልያን ዳርቻ የተሰሙ አሰቃቂ የስደት ታሪኮች የችግሩ አስከፊነት ማሳያዎች ነበሩ።

ሰለሞን ሙጩ

ማንተጋፍቶት ስለሺ 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW