1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል መልቀቅያን ያለፉ ተማሪዎች 5.4% የሚሆኑት ብቻ ናቸዉ ተባለ

ሰኞ፣ ጳጉሜን 4 2016

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ከውሰዱ 684,205 ተማሪዎች መካከል 36,409 ወይም 5.4% የሚሆኑ ተማሪዎች ማለፋቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። በመላው ሀገሪቱ 1363 ትምህርት ቤቶች ዉስጥ ምንም ተማሪ እንዳላለፈ የትምህርት ሚንስትር ፕሮፊሰር ብርኃኑ ነጋ ተናግረዋል። የተማሪዎቹ ውጤት ዛሬ ከእኩለ ሌሊት ጀምሮ ይፋ ይሆናል ተብሏል።

 የኢትዮጵያ የትምህርት ሚንስትር ፕሮፊሰር ብርኃኑ ነጋ
የኢትዮጵያ የትምህርት ሚንስትር ፕሮፊሰር ብርኃኑ ነጋምስል Education Ministry of Ethiopia

ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል መልቀቅያን ያለፉ ተማሪዎች 5.4% የሚኖኑት ናቸዉ ተባለ

This browser does not support the audio element.

ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል መልቀቅያን ያለፉ ተማሪዎች 5.4% የሚሆኑት ብቻ ናቸዉ ተባለ 

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከውሰዱ 684,205 ተማሪዎች መካከል  36,409  ወይም 5.4% የሚሆኑ ተማሪዎች ማለፋቸውን ትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ ሰኞ ጳጉሜን 4 ቀን 2016 ዓ.ም በሰጠው መግለጫ አስታወቀ።  በመላው ሀገሪቱ 1363 ትምህርት ቤቶች ዉስጥ ምንም ተማሪ አላማለፉን የተናገሩት የትምህርት ሚንስትር ፕሮፊሰር ብርኃኑ ነጋ፤ የተማሪዎች ውጤት ዛሬ ከእኩለ ሌሊት ጀምሮ ይፋ ይደረጋል ብለዋል። የዘንድሮው ብሔራዊ ፈተና በቅይጥ ማለትም በወረቀት እና በኦንላይን መሰጠቱ ይታወሳል።
 
ዛሪ ከቀትር በኋላ መግልጫ የሰጡት የትምህርት ሚንስትር ፕሮፊሰር  ብርኃኑ ነጋ በ2016 ለፈተና ከተቀመጡት 684,205  ተማሪዎች መካከል 34 409 የሚሆኑት ተማሪዎች  ብቻ ማለፋቸውን ተናግረዋል።  በሀገር አቀፍ ደረጃ  1363 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ ማሳለፍ የተሳናቸው ናቸዉ ተብሏል። በክልል ደረጃ  ኦሮሚያ 553 ሶማሊያ 156  አማራ 56 ትግራይ 52 ቤንሻንጉል 36 አፋር 33 አዲስ አበባ 4 ትምህርት ቤቶች ምንም ተማሪ ያላለፉ ናቸው  ብለዋል። 


ለ 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተማሪዎቻቸውን ለፈተና  አስቀምጠው ሁሉም የማለፊያ ነጥብ ያስመዘገበው ክልል የሀረሪ ክልል ብቻ ሲሆን፤ በዘንድሮ  ብሔራዊ ፈተና በአጠቃላይ 2 ሴት ተማሪዎች  ከአዲስ አበባ ከፍተኛውን ነጥብ አስመዝግበዋል ተብሎዋል። ከ 600 በተፍጥሮ ሳይንስ 575 ያገኛችው  የካቴድራል  ተማሪ ስትሆን፤ በማህበራዊ ሳይንስ  ደግሞ 538 ነጥብ ያመጣችው የኢትዮ ፓረንት ትምህርት ቤት ተማሪ መሆንዋ ተነግሮዋል። በትግራይ ክልል ከ 700 በታረመው የ 12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና  አንድ ተማሪ 675 በማግኘት በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ ግዜ  ከፍተኛውን ውጤት ማስመዝገቡ ተናግረዋል። በአጠቃላይ በዚህ ዓመት ከ 500 እና ከ 600  በላይ ያመጡ ተማሪዎች  1221  መኖናቸውንም የትምህርት ሚኒስትሩ አክለዋል። 
ዘንድሮ ብሔራዊ ፈተና ከተቀመጡ  684,205  ተማሪዎች መካከል 647, 796 ወይም 94 % የሚሆኑ ተማሪዎች ብሔራዊ  ፈተናውን ወድቀዋ። በመሆኑምል በትምህርት ሚኒስቴር ለአንድ ግዜ ብቻ በሚል  የተጀመረው ውጤታቸው ዝቅተኛ ለሆነ ተማሪዎች የሚሰጠው  የሬሜዲያል ፕሮግራም ዘንድሮ  እንደሚኖር የትምህርት ሚኒስቴር ብርኃኑ ነጋ ገልጸዋል። 

ሃና ደምሴ 
አዜብ ታደሰ 
ነጋሽ መሐመድ 
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW