1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዘጠነኛው የቻይናና ዓፍሪካ የትብብር ጉባኤ በቤጂንግ

ዓርብ፣ ጳጉሜን 1 2016

ፕሬዝዳንት ቺ ባሰሙት ንግግር፤ በቀጣይ ቻይና ለአፍሪካ የምትሰጠውን ድጋፍ በመቀጠል በሚቀጥሉት ሶስት አመታት ለተለያዩ የልማት ፕሮግራሞችና የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ማስፈጸሚያ 51 ቢሊዮን ዶላር የመደበች መሆኑን በመግለጽ ተግባራዊ የሚሆኑ አስር የልማት ግቦችንም ይፋ አድርገዋል

የቻይናና የአፍሪቃ የመሪዎች ጉባኤ የሁለቱን ወገኖች ወዳጅነት ለማጠናከር ይረዳሉ የተባሉ ስምምነቶች ተደርገዉበታል
ቤጂንግ።የቻይናና የአፍሪቃ ፎረም ዘጠነኛዉ የመሪዎች ጉባኤ ላይ የ50 የአፍሪቃ ሐገራት ተወካዮች ተካፍለዋልምስል Zhai Jianlan/picture alliance/Xinhua News Agency

ዘጠነኛው የቻይናና ዓፍሪካ የትብብር ጉባኤ በቤጂንግ

This browser does not support the audio element.

 

በቤጂንግ-ቻይና ዉስጥ የተደረገዉ ዘጠነኛው የቻይናና ዓፍሪካ የትብብር ጉባኤ ዛሬ ተጠናቋል። እ እ እ በ2000 አም የተመሰረተው የቻይናና አፍርካ የትብብር ፎረም፤ ጉባኤውን በየሶስት አመቱ የሚያካሂድ ነዉ።የዘንድሮው ጉባኤ ካለፈው ዳካር-ሴኔጋል ከተካሄደው ጉባኤ የሚበልጥና  ኢትዮጵያን ጨምሮ ካምሳ በላይ የፍርካ አገሮች የተወከሉበት፣ የተለያዩ ድርጅቶች የተካፈሉበትም ነዉ።

የቻይናው መሪ ሚስተር ሺ ጄንፒንግ ጉባኤውን ሲከፍቱ ባደረጉት ንግግር፤ አለማቀፋዊው ስራት ፍትሀዊነት እንደሚጎለውና አገሮችንና ህዝቦችን በዕኩልነት እይደማያይ ጠቅሰው፤  ቻይናና አፍርካ ይህን ለማስተካከል በጋራ መስራት ያለባቸው መሆኑን በማንሳት መንግስታቸው ከቻይና ጋር የዲፖሎማሲ ግንኑነት ካላቸው የዓፍሪካ አገሮች ጋር ያለውን ግንኙነት ወደ ስትራጄካዊ ደረጃ የሚያሳድግ መሆኑን  አስታውቀዋል።
የቻይና ገበያ ለአፍሪካ ክፍት ስለመሆኑና የታሪፍ መነሳት  
ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው  አክለውም፤ አገራቸው ከአፍሪካ ጋር ያለውን ንግድ ለማስፋትና መዛባቱንም ለመቀነስ፤ ክቻይና ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኑነት ላላቸው የአፍርካ አገሮች ገበያዋን ክፍት ለማድረግ የወሰነች መሆኑን አስታውቀዋል። “ ቻይና በፈቃደኝነት ገበያዋን ለአፍሪካ ክፍት ታደርጋለች። 33 የአፍርካ አገሮችን ጨምሮ ከቻይና ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ላላቸው በዝቅተኛ የዕድገት ደረጃ ለሚገኙ አገሮች የንግድ ሸቀጦች ላይ ምንም አይነት ቀረጥ እንዳይጣል ወስነናል” በማለት ይህም በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለውን የንግድ መዛባት ለመቀነስ እንደሚረዳ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።፡
ቻይና  ለአፍሪካ 51 ቢሊዮን ዶላር መመደቧ
ፕሬዝዳንት ቺ  ባሰሙት ንግግር፤ በቀጣይ ቻይና ለአፍሪካ የምትሰጠውን ድጋፍ በመቀጠል በሚቀጥሉት ሶስት አመታት  ለተለያዩ  የልማት ፕሮግራሞችና የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ማስፈጸሚያ  51 ቢሊዮን ዶላር የመደበች መሆኑን በመግለጽ ተግባራዊ የሚሆኑ አስር የልማት ግቦችንም ይፋ አድርገዋል ።፡ ባስሩ የተግባር እቅድ፤ የህዝብ ለህዝብ ግንኑነት፣ የንግድ መሳለጥ፤የእርሽና እንዱስትሪ መስፋፍት፤ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች፤ የትምህርትና ጤና የሮግራሞችና ለሎችም የልማት ፕሮግራሞች የሚካተቱ ስለመሆኑም ተገልጿል።

ጉባኤው በመጨርሻም፤ የቢጂንጉን የጋራ መግለጫ በማውጣትና የአስሩን የልማት እቅዶች በማጽደቅ በስኬት የተጠናቀቀ መሆኑ ታውቋል። ከጉባኤው ጎን ለጎ የኢትዮጵያውን ጠቅላይ ሚኒስተር  ዶክተር አቢይ አህመድን ጨመሮ ብዙዎቹ የአገር መሪዎች ከፒረዝዳንት ሺ ጋር ተገናኝተው በሁለትዮሽ ጉዳዮችም እንደመከሩና በበርካታ የልማት ፕሮግራሞች ላይም የጋራ መግባቢያ ስነዶችን እንደተፈራረሙም ታውቋል።
በቻይናና አፍርካ የትብብር ፎረም ላይ የሚሰሙ ትቶችና ክርክሮች

የዘጠነኛዉ የቻይናና የአፍሪቃ ሐገራት የመሪዎች ጉባኤ ተካፋዮች በከፊልምስል Andy Wong/AP/picture alliance

የቻይናንና አፍሪካ የትብብር ፎረም ሁለቱንም ወገኖች በዕኩል ተጠቃሚ እያደረገ ስለመሆኑ የሚነሳ ጥያቄ አለ። ለቻይና  ይህ የትብብር ማዕቀፍ የአፍሪካን ገበያ የከፈተላት፤ ርካሺ የጥሬ ሀብት ያስገኝላት፤ በዓለማቀፉ መድረክም ድጋፍ ያሰባሰበላት ነው በማለት ጥቅሙ ለቻይና ያደላ ነው የሚሉ ያሉትን ያህል፤  ሌሎች ለምሳሌ  በጆሀንስበርግ  ዩንቨርስቲ የቻይናና አፍሪካ ጥናት ማዕከል ዳይሬክተር የሆኑት ፕሮሰፌርር ዳቪድ ሞንያየን የመስሉ ደግሞ በቻይና ላይ የሚቀርበው ወቀሳና ክስ ከመዕራባውያኑ የቅኝ ገዥነት ታሪክ ጋር  የተያያዘ ነው በማለት ይከራከራሉ፤ “ ለብዙዎቹ የምዕራብ አገሮች፤  የአፍሪካ አገሮች  የቀድሞ ግኝ ግዛቶች በመሆናቸው የቻይናን በእነዚህ አገሮች በስፋት መገኘት አይፈልጉትም” በማለት በንግድ መዛባትም ሆነ በብድር ጫና ምክኒያት በሚከሰቱ ችግሮች ላይ ግን ሁለቱ ወገኖች መደራደርና መወያየት እንድሚኖርባቸው አገንዝበዋል።
የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሀፊ ስለ ጉባኤውና የቻይናና አፍሪካ ግንኙነት

ከግራ ወደ ቀኝ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አሕመድና የቻይና ፕሬዝደንት ሺ ቺፒንግ ምስል Yin Bogu/Xinhua/IMAGO

በጉባኤው በእንግድነት የተገኙት የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥም  ጉባኤውንም ሆነ የቻይናንና አፍርካን ግንኙነት ባጠቃላይ፤  አራያነት ያለው ሲሉ ነው የገለጹት፤ “  የቻይናና  አፍሪካ  ግንኙነት የደቡብ -  ደቡብ ትብብር አይነተኛ ምሳሌ ነው ። በትብብሩ ማዕቀፍ  ቻይና የምታደርገውና እይደረገች ያለው፤  አፍሪካ በመሰረተ ልማት ያለባትን ክፈተት፤ በትምህርት ያለባትን ከፍተት፤ በጤና ያለባትን ክፍተት  ለመሙላት የሚረዳ ነው” በማለት ትብብሩ ይልቁንም አፍሪካ የ2030 የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳክት የሚያግዝ ጥሩ እድል መሆኑን ገልጸዋል።
ገበያው ንጉሴ
ነጋሽ መሐመድ

እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW