በአማራ ክልል የተራዘመው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እና አንድምታው
ቅዳሜ፣ ጥር 25 2016![Äthiopien Volksrepräsentantenhaus](https://static.dw.com/image/66144719_800.webp)
ማስታወቂያ
በአማራ ክልል የተፈጠረውን የሰላም መደፍረስ ተከትሎ የተወካዮች ምክር ቤት ሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ ም ለስድስት ወራት የሚዘልቅ የአስቸኳ ጊዜ አዋጅ አፅድቋል፡፡ ምክር ቤቱ የጊዜውን መጠናቀቅ ተከትሎ ትናትን ባደረገው ልዩ ስብሰባ አዋጁ ለሌላ 4 ወራት እንዲራዘም ዉሳኔ አስተላልፏል፡፡በአማራ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ድንጋጌው ተራዘመ የአዋጁን መራዘም በተመለከተ በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች የሚገኙ አንዳንድ ነዋሪዎች የአዋጁን መራዘም ሲኮንኑ ሌሎች ደግሞ በአዎንታዊ መልኩ ተመልክተውታል፡፡ አስተያየት ሰጪዎቹ ሌሎች አማራጮች መታየት እንደነበረባቸውም አመልክተዋል፡፡
ዓለምነው መኮንን
ታምራት ዲንሳ