1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዜና፣ የጀርመን መንግስት 400 ሚሊዮን መደበ፣ ቻይና ዉስጥ ጎርፍ 25 ሰዉ ገደለ

ረቡዕ፣ ሐምሌ 14 2013

ለአስቸኳይ ርዳታ ከተመደበዉ 400 ሚሊዮን ዩሮ የፌደራል መንግሥቱ ግማሹን ሲያወጣ፣ በአደጋዉ የተጎዱት የኖርድ ራይን ቬስትፋሊያ እና የራይንላንድ ፋልስ ክፍለ-ግዛቶች ቀሪዉን 200 ዩሮ ያዋጣሉ።በሁለቱ ግዛቶች ባለፈዉ ሳምንት ለተከታታይ ሶስት ቀናት የጣለዉ ዝንብ ያስከተለዉ ጎርፍ የገደላቸዉ ሰዎች ቁጥር ከ170 በልጧል

China Zhengzhou | Starke Regenfälle | Verwüstungen
ምስል Chinatopix/AP/picture alliance

ዜና፣ኃምሌ14፣2013

This browser does not support the audio element.

የጀርመን መንግሥት በጎርፍ ለተጥለቀለቁ አካባቢ ነዋሪዎች መርጃ 400 ሚሊዮን ዩሮ መደበ።የጀርመን የሚንስትሮች ምክር ቤት (ካቢኔ) ዛሬ ባሳለፈዉ ዉሳኔ መሰረት ገንዘቡ በጎርፍ ለተጎዳዉ ሕዝብ ያለብዙ የቢሮ ዉጣ ዉረድ ባስቸኳይ የሚሰጥ ነዉ።የገንዘብ ሚንስትር ኦላፍ ሾልስ ለጋዜጠኞች እንደነገሩት የርዳታዉ ገንዘብ አደጋዉ በደረሰባቸዉ በሁለት ክፍለ-ግዛቶች አማካይነት ለጉዳተኞች ይደርሳል።«ለሚፈልጉ በሙሉ አሁን አስቸኳይ ርዳታ ያገኛሉ።ርዳታዉ አስፈላጊ በሆነበት መጠን፣ አደጋዉ በደረሰባቸዉ ክፍለ-ግዛቶች አማካይነት ካለምንም የቢሮካራሲ ዉጣ ወረድ ይከፋፈላል።ዳግም ግንባታዉ፣ ብዙ ቢሊዮን ዩሮ እና ምናልባት ዓመታት መጠየቁ አይቀርም።ይሁንና አሁኑኑ መጀመር እንችላለን።በዳግም ግንባታዉ ሒደት የሚገጥሙ ፈተናዎችን ከክፍለ-ግዛት አስተዳደሮች ጋር ለመጋፈጥ ዝግጁ ነን።ሁሉም ሰዉ በዚሕ መተማመን ይችላል።ይሕ የፖለቲካ ፍላጎታችን ነዉ።»
ለአስቸኳይ ርዳታ ከተመደበዉ 400 ሚሊዮን ዩሮ የፌደራል መንግሥቱ ግማሹን ሲያወጣ፣ በአደጋዉ የተጎዱት የኖርድ ራይን ቬስትፋሊያ እና የራይንላንድ ፋልስ ክፍለ-ግዛቶች ቀሪዉን 200 ዩሮ ያዋጣሉ።በሁለቱ ግዛቶች ባለፈዉ ሳምንት ለተከታታይ ሶስት ቀናት የጣለዉ ዝንብ ያስከተለዉ ጎርፍ የገደላቸዉ ሰዎች ቁጥር ከ170 በልጧል።አብዛኛዉ ሰዉ የሞተዉ ከዚሕ ዶቸ ቬለ ከሚገኝበት ከቦን በጥቂት ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ በሚገኘዉ አሕርቫይለር በተባለዉ አካባቢ ነዉ።ጎርፍ ቤልጂግም ዉስጥ ከ30 በላይ ሰዎች ገድሏል።ከሞቱት ሌላ በብዙ መቶ የሚቆጠሩ ሰዎች ያሉበት አልታወቀም።ከጀርመንና ከቤልጂግ በተጨማሪ ኔዘርላንድስን፣ ላክሰምበርግን፣ ኦስትሪያ፣ ስዊትዘርላንድና ቼክ ሪፐብሊክን ያጥለቀለቀዉ ጎርፍ በብዙ ቢሊዮን ዩሮ የሚገመት ንብረት አዉድሟል።መንገዶችን፣ ድልድዮችን፣ ሐዲዶችን የመብራት፣ የዉኃና የስልክ መስመሮችን አበላሽቷል።በሌላ የጎርፍ ዜና የቻይናን ማዕከላዊ ግዛት ሔናንን ያጥለቀለቀ ጎርፍ በትንሽ ግምት 25 ሰዎች ገደለ፤በብዙ መቶ ሺሕ የሚቆጠሩ አፈናቀለ።የአደጋ ሠራተኞች እንዳስታወቁት ከሟቾቹ ገሚሱ የሞቱት ሔናን ግዛት ርዕሠ-ከተማ ዤንግዡዉ ዉስጥ በባቡር ሲጓዙ በደራሽ ዉሐ ተዉጠዉ ነዉ።የአየር ንብረት አጥኚዎች እንደሚሉት የሔናን ግዛትን ከፊል አካባቢዎች ያጥለቀለቀዉ ጎርፍና የመሬት መደርመስ የደረሰዉ በአካባቢዉ ከአንድ ሺሕ ዓመት ወዲሕ ታይቶ የማይታወቅ ከባድ ዝንብ ከጣለ በኋላ ነዉ።ጎርፉ 12 ሚሊዮን ሕዝብ የሚኖርባትን የዤንግዡዉ ከተማ የመንገድ፣የመብራት፣የዉኃና የስልክና መስመሮችን በጣጥሷል።የአደጋ ሠራተኞና ሕዝብ ለመርዳት የዘመተዉ ጦር  ከ2 መቶ ሺሕ የሚበልጥ ሕዝብ በጎርፍ ከተጥለቀለቀዉ አካባቢ ማሸሽ ችለዋል።ፕሬዝደንት ሺ ጂንፒንግ ባስተላለፉት መልዕክት «በጣም አሰቃቂ» ያሉትን ጥፋት ለመከላከል የመንግሥታቸዉ ባለስልጣናት አበክረዉ መጣር አለባቸዉ።

ምስል Hou Jianxun/dpa/picture alliance

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW