ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች አጠቃቀም ለተማሪዎች ጠቃሚ ወይስ ጎጂ?
ዓርብ፣ መስከረም 30 2018
በቅርቡ የ ኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር ማህበራዊ ሚዲያ ገጽ ከፍተው የሚጠቀሙ ተማሪዎች በማህበራዊ ሚዲያው በመሳብ የትምህርታቸው ትኩረት ያጣሉ በሚል ተማሪዎች የማህበራዊ ሚዲያ ገጽ (አካውንት) እንዳይኖራቸው የሚል ሃሳብ አቅርባል፡፡
የበርካታ ተማሪዎች ውጤት በእጅጉ ወድቋል በሚባልበትና ትኩረታቸውን ከሰረቁ ነጥቦች አንዱ የማህበራዊ ሚዲያው አጠቃቀም ነው በሚባልበት በአሁን ወቅት ጉዳዩ ማነጋገሩ የማይቀር ነው፡፡
የማህበራዊ ሚዲያ ጉዳቱ ወይስ ጥቅሙ ያይላል? ተማሪዎችስ በህግ ከማህበራዊ ሚዲያ ገጽ ቢታቀቡ ጥቅሙ ወይስ ጉዳቱ ያመዝናል በሚለው ሃሳብ ላይ ክርክር አድርገናል፡፡ የሚሟገቱት የ11ኛ ክፍል ተማሪ የሆኑ ሁለት ተማሪዎች ናቸው፡፡ የ16 ዓመት ታዳጊ ያብስራ ሙላቱ እና የ17 ዓመት ታዳጊ ሜላት ንጉስ።
ተማሪ ያብስራ የ ማህበራዊ ሚዲያ ተጽእኖ እና ጥቅሙ እጅግ በላቀበት በአሁን ወቅት ተማሪዎች ከዚህ ሊያገኙ የሚችሉትን እና ማግኘትም የሚገባቸውን ጥቅም ስለሚያሳጣቸው ተማሪዎች በስነምግባር እና በአግባቡ ኃላፊነት ተሰምቷቸው የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾችን ከፍተው እንዲጠቀሙ ማድረጉ እንጂ በህግ መገደቡ አላስፈላጊ ነው ስትል፤
ተማሪ ሜላት ደግሞ የተማሪዎችን ትኩረት በመስረቅ ለትምህርት ጥራቱ ነቀርሳ እየሆነ የመጣው የማህበራዊ ሚዲያ ላይ ተማሪዎች ገጽ በመክፈት አንዳይጠቀሙ ማድረግ በህግም ጭምር መደገፍ እንደሚጋባ ታምናለች፡፡
የዶይቼ ቬለ የዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች የአዲስ አበባ አቅራቢ ሱመያ ሳሙኤል አወያይታቸዋለች።