ማስታወቂያ
በኦን ላይን በወሰደችው የሥዕል ሥልጠና ከሥሜት መግለጫነት ባለፈ የገቢ ምንጭ እንደሆናት የጠቀሰችው አቢጌል በአሁኑ ወቅትም ለተለያዩ ቤተሰቦችና ድርጅቶች ሥዕሎችን በክፍያ እንደምትስል ገልጻለች፡፡ በኢትዮጵያ የሥዕል ጥበብ ብዙም ትኩረት ያልተሰጠው የኪነ ጥበብ ዘርፍ መሆኑን የምትናገረው አቢጌል “ አሁን ላይ የሥዕል ሥሜት ከእኔ አልፎ ቤተሰቦቼም አንዲጋሩት አድርጊያለሁ ፡፡ በቀጣይ በዚህ ሙያ የራሴን አሻራ ለማሳረፍ እቅድ አለኝ ፡፡ ሌሎች ወጣቶች ለራሳቸው ጊዜ በመስጠት እንደየዝንባሊያቸው ጥረት ማድረግ አለባቸው “ ብላለች ፡፡
#ዝምታሰባሪአዳጊሴቶች #GirlzOffMute
ዘገባ: ሊሻን ዳኜ
ቪድዮ: ሸዋንግዛው ወጋየሁ
