1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የ«ስትሪንግ አርት»ተሰጥዎ ያላቸው ቤዛዊት እና ናርዶስ

ዓርብ፣ የካቲት 26 2013

የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎቹ ቤዛዊት ታምሩ እና ናርዶስ አማከለ ባለቀለማት ክሮችን በመጠቀም ስትሪንግ አርት የተባሉ ስዕሎችን የመስራት ተስጥኦ አላቸው። ወጣቶቹ የክር ስዕሎችን ሲጀምሩ እንደመዝናኛ ወይም ሆቢ ቢሆንም ቀስ በቀስ ግን ወደ ንግድ እየቀየሩት እንደሚገኙ ይናገራሉ። የዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች ዘጋቢ ሊሻን ዳኜ ከእነሱ ጋር ቆይታ አድርጋለች።  

Girlz Off Mute | String art gifted girls
ምስል Shewangizaw Wegayehu/DW

የ«ስትሪንግ አርት»ተሰጥዎ ያላቸው ቤዛዊት እና ናርዶስ

This browser does not support the audio element.

የ12 ኛ ክፍል ተማሪ የሆኑት ቤዛዊት እና ናርዶስ ይህን ጥበብ በመጠቀም በጠፍጣፋ ጣውላ ላይ ባለቀለማት ክሮችን በመጠቀም በተጥሮዋዊ፣ ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ስዕሎችን ያዘጋጃሉ። «መጀመሪያ ላይ ስለ ስትሪንግ አርት ኢንተርኔት ላይ ነው መረጃውን ያገኘነው። ስንጀምር ብዙ እንሰራለን ብለን አልነበረም። ለጓደኛችን ስጦታ ለመስጠት ብለን ነው የሞከርነው» ትላለች ናርዶስ። ቤዛዊት ቤተሰቦቻቸው እየደገፏቸው እንደሆነ ትናገራለች« ትዛዝ ካለን በዕረፍት ጊዜያችን እንሰራለን» ትላለች። ሰዎች ስራችንን ያደንቁልናል የሚሉት እነዚህ ወጣቶች ከሚገዛው ሰው ይልቅ ስራቸውን የሚያደንቅላቸው ሰው እንደሚበልጥ ይናገራሉ። አሁን አሁን በትዕዛዝ ይሰራሉ፣ ይሸጣሉ። ወደፊትም በዚህ ችሎታቸው ሊገፉበት ይፈልጋሉ።

የ«ስትሪንግ አርት»ተሰጥዎ ያላቸው ቤዛዊትና ናርዶስ

04:02

This browser does not support the video element.

ሊሻን ዳኜ
ሸዋንግዛው ወጋየሁ/ልደት አበበ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW