1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: በአፍላ እድሜ ላይ ያሉ ሴቶች ለምን ራሳቸውን ያጠፋሉ?

04:27

This browser does not support the video element.

ማክሰኞ፣ መስከረም 28 2017

በአፍላ እድሜ ክልል የሚገኙ ወጣት ሴቶች ራሳቸውን አጠፉ ሲባል መስማት አሁን አሁን እየተለመደ መጥቷል። የዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች መሰናዶ ዘጋቢ ብሌን ድልአርጋቸው (ድሬደዋ) ከሶስት ጓደኞቿ ጋር አፍላ ወጣት ሴቶች ራሳቸውን አጠፉ ሲባል የሚሰማባቸውን ምክንያቶች እና መፍትሄ ባሏቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በትምህርት ውጤታማ የሆኑ ወጣት ሴቶች የሚጠብቁት ውጤት አለማምጣት ፣ ቤተሰብ በአፍላ እድሜ ለሚገኙ ሴት ልጆቹ የሚሰጠው ትኩረት አናሳ መሆን እና በተለያየ መልኩ ባልበሰለው እድሜ ከተቃራኒ ፃታ ጋር የሚጀምሩት የፍቅር ግንኙነት የሚያስከትለው አሉታዊ ተፅዕኖ ህይወት የማጥፋት ያልተገባ ውሳኔ ለመወሰን ሊዳርጉ የሚችሉ ገፊ ምክንያቶች መሆናቸውን አንስተዋል።

አሁን አሁን ኃላፊነት በጎደለው መልኩ ሲተገበር በሚታየው የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም አንዳንድ ጊዜ ወጣት ሴቶች አደባባይ እንዳይወጣ የሚፈልጉት የራስ ሚስጥራቸው አደባባይ ወጥቶ ማየታቸው ለእደዚህ ዓይነት ውሳኔ ሊመራቸው እንደሚችልም በውይይቱ ተነስቷል።

ብሌን ከጓደኞቿ ጋር ባደረገችው ውይይት ከእንዲህ ያለው በአፍላ እድሜ ህልምን መና ከሚያስቀር ድርጊት ለመጠበቅ ይጠቅማሉ ያሏቸውን የመፍትሄ ሀሳቦችንም ገልፀዋል ።
#ዝምታሰባሪአዳጊሴቶች #GirlzOffMute


ዘገባ፡ ብሌን ድልአርጋቸው
ቪዲዮ፡ መሳይ ተክሉ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW