1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ባህሎቻችን በአዳጊ ሴቶች አይን

ዓርብ፣ ነሐሴ 26 2015

በዓላትን በጋራ ማክበር ፣ እቁብ በመሰብሰብ በኢኮኖሚ መደጋገፍ ፤ እንዲሁም ለቅሶ የመሳሰሉ ችግሮች ሲያጋጥሙ በዕድር አማካኝነት ሐዘንን መጋራት አብሮነትን የሚያጠናክሩ እሴቶች እንደሆኑ ታዳጊ ረድኤት እና ናዝራዊት ይገልጻሉ፡፡

ሊሻን ዳኜ እና ተወያዮቿ
ሊሻን ዳኜ እና ተወያዮቿምስል DW

ባህሎቻችን በአዳጊ ሴቶች አይን

This browser does not support the audio element.

በሀዋሳ ከተማ ነዋሪ የሆኑት የ15 ዓመቷ ታዳጊ ረድኤት አበራ እና የ17 ዓመቷ ናዝራዊት ከበደ በሚኖሩበት ማህበረሰብ ውስጥ የሚገኙ ባህላዊ ልማዶች  ሁለት አይነት መልክ አላቸው ይላሉ፡፡ ረድኤት እና ናዝራዊት ዶቼ ቬለ DW በሚያዘጋጀው የዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች ዝግጅት ጋር በነበራቸው አጭር የውይይት ቆይታ ባህላቸው በጎ ሊባሉ የሚችሉ ተግባራት የሚበዙበት ሥለመሆኑ ጠቅሰዋል ፡፡ በተለይ በዓላትን በጋራ ማክበር ፣ እቁብ በመሰብሰብ በኢኮኖሚ መደጋገፍ ፤ እንዲሁም ለቅሶ የመሳሰሉ ችግሮች ሲያጋጥሙ በዕድር አማካኝነት ሐዘንን መጋራት አብሮነትን የሚያጠናክሩ እሴቶች እንደሆኑ ታዳጊዎቹ ገልጸዋል ፡፡ ያም ሆኖ ሊቀሩ ወይም ሊሻሻሉ የሚገባቸው ልማዶች አሉ የምትለው ታዳጊረድኤት “ በተለይ በማህበረሰቡ ውስጥ ለሴት ልጅ ያለው ያልተገባ አመለካከት፣ እንዲሁም የግርዛትና የጠለፋ ድርጊቶች በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው “ ብላለች ፡፡አንደ ባህል ሊሻሻሉ የሚገባቸው ልማዶች መኖራቸውን የምትናገረው ናዝራዊት በበኩሏ “ በጊዜ አጠቃቀም ላይ ያለን ዝቅተኛ ግንዛቤ እንዲሁም ደካማ የሥራ ባህል ይስተዋልብናል ፡፡ ይህ ሊለወጥ የሚገባ አስተሳሰብ ነው “ ብላለች ፡፡

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: አልባሳቱና ታሪኮቻቸው

03:45

This browser does not support the video element.

ሊሻን ዳኜ / ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ልደት አበበ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW