1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: «አበባ አየሽ ወይ ?»

04:42

This browser does not support the video element.

ሰኞ፣ ጥቅምት 8 2014

ሴት ተማሪዎች በወር አበባቸው የተነሳ ከትምህርት ገበታቸው እንዳይቀሩ ለማበረታታት እና ለማገዝ ጉዳዮ ያገባኛል ያሉ ሶስት አስተባባሪዎች «አበባ አየሽ ወይ ?» የሚል እንቅስቃሴ ጀምረዋል።

አለማቸው በዚህ በተያዘው 2014 ዓ.ም በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች ለሚገኙ 50,000 ተማሪዎች የንጽህና መጠበቂያዎችን ማቅረብ ነው።  የንጽህና መጠበቂያ ሞዴስ መስራች የሆነችው ሚካል ማሞ እንደምትለው ከሆነ የወር አበባ መቀበያ ሞዴስ ችግር በገጠሩ የሀገሪቱ ክፍል ብቻ ያለ ሳይሆን በከተማ ውስጥም በሰፊው ይገኛል። በርካታ ሴቶችም በወር አበባ መቀበያ እጦት ምክንያት መሠረታዊ ከሆነው የትምህርት ገበታቸው ይስጓጎላሉ። ይህ ብቻ አይደለም በተለይ አዳጊ ሴቶች ስለጉዳዮ ደፍረው ለማውራት አይደፍሩም። ይህም ዝምታ እንዲሰበር እና ችግሩ ላይ እንዲሰራ ለማሳየት የዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች ዘጋቢ ሱመያ ሳሙኤል የወር አበባ መቀበያ ወደሚመረትበት ድርጅት ሄዳ ዘገባ አዘጋጅታለች።

ዘገባ: ሱሙያ ሳሙኤል
ቪዲዮ: ሰለሞን ሙጬ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW