ማስታወቂያ
የደቡብ ክልል የቅርጫት ኳስ ቡድንን በመወከል ከጉራጌ ዞን ወልቂጤ የመጣችው ሠዓዳ በውድድሩ ያሳየችው እንቅስቃሴ የብዙዎችን ትኩረት እንድታገኝ አድርጓታል፡፡ አብዛኛው የማህበረሰብ ክፍል አካል ጉዳተኞች በስፖርት ዘርፍ ይሳተፋሉ የሚል ግምት እንደሌለው የምትናገረው ሠዓዳ « ስፖርቱ ለእኔ ብዙም አልከበደኝም» ትላለች ፡፡ በቴክኒክ ሙያ ተመርቃ ስራ ያላገኘችው ሠዓዳ በአሁኑ ሰዓት ትኩረቷን ስፖርቱ ላይ አድርጋለች።
ዘጋቢ ፡ ሊሻን ዳኜ
ቪዲዮ ፡ ሸዋንግዛው ወጋየሁ