1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ትምህርት

አካል ጉዳተኝነት ያልበገረው ስኬትና ቀሪው ፈተና

05:38

This browser does not support the video element.

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 23 2015

ዘንድሮ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ2015 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን ማጠናቀቂያ ላይ ተማሪዎችን ሲያስመርቅ ትኩረት ከሳቡት ተመራቂዎች በአካል ጉዳቷ ጋር እየታገለች በሳይኮሎጂ የትምህርት ክፍል 3.3 በሆነ ከፍተኛ ውጤት በማዕረግ የተመረቀችው ዮርዳኖስ ወሮታው ትጠቀሳለች፡፡

ዘንድሮ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ2015 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን ማጠናቀቂያ ላይ ተማሪዎችን ሲያስመርቅ ትኩረት ከሳቡት ተመራቂዎች በአካል ጉዳቷ ጋር እየታገለች በሳይኮሎጂ የትምህርት ክፍል 3.3 በሆነ ከፍተኛ ውጤት በማዕረግ የተመረቀችው ዮርዳኖስ ወሮታው ትጠቀሳለች፡፡
የ22 ዓመቷ ወጣት ዮርዳኖስ ገና ከልጅነቷ ባጋጠማት ህመም ለአካል ጉዳት ተዳርጋ ብዙው ተግባሯ በቤተሰቦቿ ድጋፍ ቢከወንም፤ ባላት ብሩህ አዕምሮ ከልጅነቷ ጀምሮ በትምህርቷ ስኬታማነቷን አሳይታለች፡፡
ዮርዳኖስ ተወዳዳሪ ሆና በመገኘቷም በምርቃቷ ከአገሪቱ ርዕሰብሔር ሳህለወርቅ ዘውዴ ሽልማቷን ተቀብላ በበርካቶች አድናቆት ቢቸራትም ህይወቷስ ከምርቃቱ በኋላ እንዴት ይገፋ ይሆን?
ዮርዳኖስ አሁንም የትምህርት ስኬቷን ወደ ፊት ስለ መግፋት ታልማለች፡፡ ከትምህርቷ ስኬት ጎን ለጎን ግን በተለይም ቤተሰቦቿ የተሻለ ህክምና አግኝታ እራሷን በራሷ መርዳት የምትችልበትንም ቀን ማየት ይናፍቃሉ፡፡

#ዝምታሰባሪአዳጊሴቶች #GirlzOffMute

ዘገባ፡ ሱመያ ሳሙኤል
ቪዲዮ፡ ሥዩም ጌቱ  

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW