ማስታወቂያ
ሲሃም ጀማል ገና የሁለት ዓመት ልጅ እያለች በደረሰባት የጉሮሮ ወይም ቶንሲል ህመም ምክንያት የውድ ዐይኖቿን ብርሃን ተነጥቃ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ዐይነስውር ሆናለች።
ሲሃም የመጀመርያ ደረጃ ትምህርቷን የተማረችበት አዲስ አበባ የሚገኘው የጀርመን ስኩል ትምህርት ቤት ለዛሬ ማንነቷ በጎ አሻራ አሳርፎላታል።
ዐይነስውር መሆን ብሎም ሴት እና ወጣት መሆን የሚፈጥሩትን ጫና እየተቋቋመች ሕይወትን የምትመራው ሲሃም በተማረችበት የሕግ ሙያም ልዩ ልዩ ሥራዎችን ትሠራለች ። በዚሁ ምክንያት ወደ ተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የመጓዝ እድልም አግኝታለች።
ከሲሃም ጋር ስለ ዝንባሌዎቿ ፣ ዐይነስውርነትን ተቋቁማ ሕልሞቿን ለማሳካት ስለምታደርገው ጥረት፣ ፈተናን እንዴት ማለፍ እንደሚቻልና ከዘመኑ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ጋር እንዴት ራሷን አስማምታና ተምራ እንደምትኖር አጭር ቃለ መጠይቅ አድርገንላታል። #ዝምታሰባሪአዳጊሴቶች #GirlzOffMute
ዘገባ: ሱመያ ሳሙኤል
ቪዲዮ: ሰለሞን ሙጬ
