ማስታወቂያ
“ የሥዕል ጥበብ ሥራን ያዳበርኩት ከልጅነቴ ጀምሮ ነው “ የምትለው ወጣቷ ሥዕል በውስጧ ያለውን ችሎታዋን እንድታወጣ ብቻ ሳይሆን የገቢ ምንጭም እየሆናት እንደሚገኝ ትናገራለች ፡፡ የሥዕል ጥበብ የተለያዩ ዘርፎች እንዳሉት የተናገረችው ዱሬቲ የግድግዳ ሥዕሎችንና በትዕዛዝ በምትቀበላቸው የሰዎች ሥዕሎች ላይ ትኩረት አድርጋ እየሠራች እንደምትገኝ ጠቅሳለች ፡፡
ዱሬቲ ራሷን በሥዕል ጥበብ ለማዳበር በሀዋሳ የማሠልጠኛ ትምህርት ቤት ባለመኖሩ በወቅቱ ፍላጎቷን ለሟሟላት እንዳልቻለች ታስታውሳለች ፡፡ በዚህም የተነሳ ወደ አዲስ አበባ በመሄድ የአጭር ጊዜ ሥልጠና መውሰዷል ገልጻለች ፡፡ በሥራዎቿ ዙሪያ ቤተሰቦቿና የአካባቢው ማህበረሰብ ድጋፍ በማድረግ እንደሚያበረታቷት ተናግራለች ፡፡#ዝምታሰባሪአዳጊሴቶች #GirlzOffMute
ዘገባ: ትንቢት ሰውነት
ቪድዮ: ሸዋንግዛው ወጋየሁ
