1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰላም ባህል እና መቻቻል ውይይት

ዓርብ፣ ኅዳር 10 2014

ግጭቶችና አለመግባባቶች እንዳይከሰቱ እንዴት አስቀድሞ መከላከል ይቻላል ? ተከስተው ሲገኙስ እንዴት በውይይት መፍታት ይቻላል ? ተከስተው ሲገኙስ እንዴት በውይይት መፍታት ይቻላል?በዝግጅቱ በሀዋሳ ከተማ በአንድ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በሚገኝ የሰላም ክበብ ውስጥ ተሳትፎ እያደረጉ በሚገኙ ወጣቶች ላይ ያተኩራል።

Äthiopien | GirlzOffMute
ምስል S. Wegayehu/DW

የሰላም ባህል እና መቻቻል ውይይት

This browser does not support the audio element.

መቅደስ እና ቤተልሔም በሰላም ክበብ ውስጥ በመሳተፍ የሰላም እና መቻቻል ባህል እንዲዳብር ይሰራሩ። «ሰላም መጀመሪያ ከቤት ውስጥ ነው የሚጀምረው የምትለው» ቤተልሔም ከህፃንነቷ አንስቶ ሰላም ማስከበር ደስ እንደሚላት ትናገራለች። የክበብ አባልም የሆነችው በዚህ ምክንያት ነው። ወጣቶች በክበብ ውስጥ ያገኙትን እውቀት ሚኒ ሚዲያ ላይ እና ክፍላቸው ውስጥ ያሉ ተማሪዎችን በማካፈል ሀሳብ እንደሚለዋወጡ ይናገራሉ። መቅደስ « እኔ ለምሳሌ የክፍል አለቃ ነኝ፤  ክፍት ክፍለ ጊዜ ካለ በስብሰባ ላይ ያገኘሁትን እውቀት ማስታወሻዬን በማውጣት በዛ አማካኝነት ለሌሎች አካፍላቸዋለሁ ትላለች።»  ወጣቶቹን ያወያየችው በሀዋሳ የዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች ዘጋቢ ሊሻን ዳኜ ናት ።

ሊሻን ዳኜ
ሸዋንግዛው ወጋየሁ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW