ቴክኒክአፍሪቃዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: የፈጠራ ስራ ያቀረበች ብቸኛ ሴት03:52This browser does not support the video element.ቴክኒክአፍሪቃ12 ሚያዝያ 2014ረቡዕ፣ ሚያዝያ 12 2014በሀዋሳ ከተማ ነዋሪ የሆነችው ወጣት ቃል ኪዳን ደሳለኝ የ19 ዓመት ወጣትና የ12ኛ ክፍል ተማሪ ናት ፡፡ ተማሪ ቃል ኪዳን ሰሞኑን በሀዋሳ ከተማ በተካሄደው የሳይንስና ቴክኖሎጂ አውደ ርዕይ (ኤግዚቢሽን) ላይ ከትምህርት ቤት ጓደኞቿ ጋር በመሆን ለእይታ ያቀረበቻቸው የፈጠራ ሥራዎች አድናቆትን አስገኝተውላታል፡፡ማገናኛዉን ኮፒ አድርግማስታወቂያቃል ኪዳን ለዕይታ ካቀረበቻቸው የፈጠራ ስራዎች መካከል የህንፃ ዲዛይን እና ንብረት በሌባ ሲሰረቅ የደውል ጥሪ የሚያሰማ የፈጠራ ስራ ይገኙበታል። ወጣቷ ትምህርት ቤቷን ወክላ አውደ ርዕይ ያቀረበች ብቸኛ ሴት ተማሪ ናት። ዘገባ ፡ ሊሻን ዳኜ ካሜራ ፡ ሸዋንግዛው ወጋየሁ