ለዝግጅታችን አስተያየት የሰጡት መምህር አሸቱ ፈይሳ በትምህርት ቤቶች የሚዘጋጁ አንዳንድ ዝግጅቶች ጠቃሚ ጎን ቢኖራቸውም ወጣቶቹን "ለፆታ መሳሳብ ይዳርጋቸዋል" ፤ ይሄም ወጣት ሴት ልጆችን ያለዕድሜ ለሚከሰት እርግዝና እንዲጋለጡ ያደርጋል ብለዋል።
በትምህርት ቤቶች ስርዓተ ፆታን በሚመለከት ትምህርት ቢሰጥም ትምህርቱ ጠበቅ ባለና ተማሪው ከመሰል ችግሮች እንዴት ራስን መጠበቅ እንደሚችሉ ጠበቅ ያለ እውቀት እና ክህሎት ማስጨበጥ ላይ ድክመት ይታያል የሚሉት መምህር እሸቱ ይህም ለችግሩ መከሰት አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ጠቁመዋል።
ማንኛውም ወጣት ለአካለ መጠን በደረሰ ጊዜ የሚሰማው የፃታ ፍላጎት መነሳሳት ተፈጥሯዊ ነው ያሉት መምህር እሸቱ ይሁን እንጂ ይህንን ተፈጥሯዊ በሆነ መንገድ የመጣን የፃታ ፍላጎት መነሳሳት ለመግታት አዕምሮን መጠቀም ይገባል የሚል ምክረ ሀሳብ አንስተዋል።
በአጠቃላይ በወጣትነት እድሜ ምዕራፍ የሚገጥምን መሰል ችግር ለመከላከል የራሳቸው የወጣቶች ፣ ወላጆች ፣ ትምህርት ቤቶችና ሌሎች አካላት የበኩላቸውን ሊወጡ ይገባል የሚለው የብዙዎች የጋራ ሀሳብ ነው።
በድሬደዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ የጤና ማበልፀግ ኬዝ ቲም አስተባባሪ ሲስተር መሰሉ አጥናፌ ለዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች ዘጋቢ ሊዲያ መለስ እንዳብራሩት እድሜያቸው ድሬደዋ ውስጥ ፅንስ የሚያጨናግፉት መካከል 14 በመቶ ያህሉ እድሜያቸው ከ 18 ዓመት በታች የሆኑ ሴቶች ናቸው።
ዘገባ: ሊዲያ መለስ
ቪዲዮ: መሳይ ተክሉ