1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: ፍቅረኛ ለመያዝ ጥሩው ዕድሜ ስንት ነው?

05:33

This browser does not support the video element.

ሐሙስ፣ መስከረም 26 2015

ተፈጥሯዊውን እድገት ተከትሎ የሚመጣው የተቃራኒ ፆታ መፈላለግ ወጣቶች ለህይወታቸው አዲስ ምዕራፍ ወደሆነው የፍቅር ግንኙነት እንዲገቡ ያደርጋል። እድገቱም ክስተቱም ተፈጥሯዊ ይሁን እንጂ ለዚህ ጥሩ የሚባለው እድሜ የትኛው ነው?

በዚህ መሰሉ ሀሳብ ላይ በነፃነት የሚናገሩ ወጣት ሴቶችን ማግኘት አስቸጋሪ የነበረ ቢሆንም በድሬደዋ የሚኖሩት ፂሆን እና ጓደኞቿ ፍቃደኛ ሆነው ዝምታቸውን ሰብረዋል። ወጣቶቹ  አንዲት ሴት የወንድ ጓደኛ ልትይዝ የሚገባት  "እድሜዋ ሃያ እና ከዚያ በላይ ሲሆናት ነው" ሲሉ ተመሳሳይ የሆነ የጋራ እሳቤያቸውን አካፍለውናል። ወጣቶቹ ለሰጡት ምላሽ በምክንያትነት ያነሱት" እድሜው ሴቷም ሆነ ወንዱ ክፉና ደጉን መለየት እና ማመዛዘን የሚችሉበት መሆኑን ነው"።

እድሜያቸው ከሀያ በታች ሆኖ የወንድ ጓደኛ የሚይዙ ወይም ከተቃራኒ ፃታ ጋር ግንኙነት የሚጀምሩ መኖራቸውን የጠቀሱት ዝምታ ሰባሪዎቹ በአቻ ተፅዕኖ ወደ መሰል ሁኔታ እንደሚገባ እና የጓደኛ ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ይናገራሉ።  ከዚህም ሌላ  ከልጆቻቸው ጋር ግልፅ ውይይት የሚያደርጉ ጥቂት ወላጆች ቢኖሩም በአብዛኛው የተለመደ አለመሆኑን ያነሱት ወጣቶቹ ወላጆች ለአቅመ አዳምና ሄዋን ከደረሱ ልጆቻቸው ጋር በቅርበት መወያያት ጠቃሚ ነው ብለዋል ።
#ዝምታሰባሪአዳጊሴቶች #GirlzOffMute

ዘገባ: ሊዲያ መለስ
ቪዲዮ: መሳይ ተክሉ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW