1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: 2 መፅሀፍት ያሳተመችው ታዳጊ

05:30

This browser does not support the video element.

ማክሰኞ፣ ኅዳር 13 2015

ህሊና የሺዋስ የ9ኛ ክፍል ተማሪ ናት፡፡ 14 ዓመቷ ነው። ተወልዳ ያደገችው በአዲስ አበባ ከተማ ሲሆን የፖለቲከኛ የሺዋስ አሰፋ ልጅም ናት፡፡ ገና በለጋ እድሜዋ በተለይም በልብ ላይ በምታደርገው ምርምርና በዘርፉ ባካበተችው እውቀት የበርካቶችን ቀልብ ስባለች፡፡ ህሊና ገና በ14 ዓመት ዕድሜ ላይ ብትገኝም ባለፈው ዓመት በዚሁ በልብ ላይ ያጠነጠኑ ሁለት መጻህፍትን በመጻፍ ለማሳተም በቅታለች፡፡

የልብ ሃኪም (Cardiologist) ስለመሆን የምታልመው ህሊና ‘ANATOMY & PHYSIOLOGY OF THE HEART’ በሚል ርዕስ በእንግሊዝኛ ቋንቋ በልብ እና የልብ አሰራር ላይ የሚያጠነጥን መጽሃፏ ለአንባቢያን የበቃው ባለፈው ዓመት ነበር፡፡
በስድስት ቋንቋዎች የመግባባት ክህሎት ያላት ተዳጊዋ ገና በ13 ዓመቷ በዚሁ በባለፈው 2014 ዓ.ም. መጨረሻ በግዕዝ፣ በአማርኛ፣ በአረብኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች “ስለልብ የተነገሩ ምርጥ አባባሎች” የተሰኘ መጽሃፍም አሰናድታ ለንባብ አብቅታለች፡፡
ከእድሜዋ አንጻር በልብ ላይ የተለየ እውቀት እያዳበረች የመጣችው ህሊና የሺዋስ ለፍሬያማ አስተዳደጓ የቤተሰቦቿን ሚና በጉልህ ታነሳለች፡፡
በኢትዮጵያ ያለው የልብ ህክምና ውስንነቶች በዘርፉ አገሯን ለማገልገል እንዳነሳሳትም በመግለጽ በሙያው ትልቁን የራሷን አሻራ ስለማሳረፍ ታልማለች፡፡ ህሊና በዚህ በህክምና በተለይም በልብ ህክምና ላይ እያዳበረች ካለችው እውቀት በተጨማሪም በስዕል ክህሎት የጎላ ብቃት አላት፡፡
የዶይቼ ቬለ ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች ዘጋቢ ሱመያ ሳሙኤል ከህሊና የሺዋስ ጋር ለቃለምልልስ ተቀምጣ ነበር፡፡ #ዝምታሰባሪአዳጊሴቶች #GirlzOffMute

ዘጋቢ: ሱመያ ሳሙኤል
ቪዲዮ ፡ ሥዩም ጌቱ 
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW