1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: የክብደት ስፖርት አፍቃሪዋ ብሩክታዊት

05:08

This browser does not support the video element.

ረቡዕ፣ ጥር 22 2016

ብሩክታዊት ፍቅሬ የ 17 ዓመት ታዳጊ እና የ 11 ኛ ክፍል ተማሪ ናት። ታዳጊዋ ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይም በሴቶች ዘንድ ብዙም ያልተለመደ የስፖርት ዘርፍ ላይ በመሳተፍ ራሷን ትልቅ ደረጃ ላይ ለማድረስ ጥረት ጀምራለች። 

ብሩክታዊት በውጭው ዓለም ከፍተኛ ተቀባይነት ያለው የሰውነት ማነጽ ወይም ግንባታ ( Body Building ) ላይ አተኩራለች። የሰውነት ግንባታ - የቅርጽ ውድድር ኢትዮጵያ ውስጥ በሴቶች ቀርቶ በወንዶችም ያልተለመደ ቢሆንም ታዳጊዋ ግን ሥራዬ ብላ ተያይዛዋለች።

ብሩክታዊት ይህንን የሰውነት ቅርጽ ግንባታ ስፖርት መሥራትን ስታስብና ስትጀምር ከሚያበረታታት ይልቅ ነቀፌታ እና አሉታዊ አስተያየት የሚሰጣት ይበዛ እንደነበር ታስታውሳለች። እንዲህ ያለው ነቀፌታ በቅርብ ከሚያውቋት ሰዎችም ይሁን በማህበራዊ መገናኛዎች ከሚያዩዋት ተደጋግሞ እንደመጣባትም ገልጻለች።

ታዳጊዋ ብሩክታዊት የስፖርት ሥራዋ ከትምህርቷ ጋር እንዳይጋጭ በጥንቃቄ ሰዓት በመመደብ እየሠራች ትገኛለች። ወደፊት ሀገር ውስጥ የክብደት ማንሳት እንዲሁም የሰውነት ቅርጽ ውድድሮች ሲደረጉ የመሳተፍ፣ አለፍ ሲልም በዓለም መድረክ በሚዘጋጁ መሰል ውድድሮች ላይ ሀገሯን የመወከል ውጥን ይዛለች። #GirlzOffMute, #ዝምታሰባሪአዳጊሴቶች

ዘገባ፤ ሱመያ ሳሙኤል 
ቪዲዮ፤ ሰለሞን ሙጬ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW