1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: የፈጠራ ሥራ አቅራቢዋ ተማሪ

04:47

This browser does not support the video element.

እሑድ፣ ግንቦት 18 2016

ተማሪ መቅደስ አስፋው በያዝነው የሳምንቱ መጨረሻ በሀዋሳ ከተማ በተዘጋጀው የሳይንስና የፈጠራ ሥራዎች ኤግዚቢዥን ላይ ሥራዎቻቸውን ካቀረቡት ተማሪዎች መካከል አንዷ ናት ፡፡ የ9ኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው መቅደስ የፈጠራ ሥራዎቿን ያቀረበችው የወዳደቁ የውሃ ፓስቲክ ኮዳዎ ችና የተጣሉ ወረቀቶችን በመጠቀም መሆኑን ትናገራለች ፡፡ ያገለገሉ ቁሳቁሶችን በመጠቀም የቤት ውስጥ መገልገያና ማስዋቢያዎችንም በመሥራት ለእይታ አቅርባለች ፡፡

የውሃ ፓላስቲክ ኮዳዎችንና የተጣሉ ወረቀቶችን ለሥራዋ ለመጠቀም ያነሳሳት ለአካባቢ ጥበቃ በመቆርቆር መሆኑን የጠቀሰችው ተማሪ መቅደስ “ በተለይም እነኝህ ያገለገሉ ፕላስቲኮች በየቦታው ሥለሚጣሉ የውሃ መውረጃ ቱቦዎችን በመድፈን የጎርፍ አደጋ እንዲፈጠር ሲያደርጉ ይስተዋላል ፡፡ እነኝህን ፕላስቲኮች መልሰን ለተለያዩ ነገሮች መጠቀም እንደምንችል ለማሳየት ነው “ ብላለች ፡፡
 የሳይንስና የፈጠራ ሥራዎች ኤግዚቢዥን ተሳታፊዋ ተማሪ መቅደስ የዐውደ ርዕዩ ጎብኚዎች የሚያበረታቱ በጎ አስተያየቶችን እንደሰጧትና ጓደኞቿና ወላጆቿም በሥራዋ እንደሚያበረታቷት ነግራናለች። ተማሪ መቅደስ በቀጣይ ከወዳደቁ ዕቃዎች ሌሎች ተጨማሪ ሥራዎችን የመሥራት ሀሳብ እንዳላትም ጠቅሳለች። 
#ዝምታሰባሪአዳጊሴቶች #GirlzOffMute

ዘገባ: ሊሻን ዳኜ
ቪድዮ: ሸዋንግዛው ወጋየሁ  
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW