1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: ባለራዕይዋ አትሌት

05:35

This browser does not support the video element.

ረቡዕ፣ ሐምሌ 3 2016

በሀዋሳ ከተማ በተካሄደው 12ኛው ከ20 ዓመት በታች የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ባሳየችው የጎላ ተሳትፎ የብዙዎችን ትኩረት ስባለች ፡፡ የ19 ዓመት ወጣቷ ራሄል ተስፋዬ ፡፡ ራሄል በሻምፒዮናው ከተለያዩ ክልሎች ከመጡ ተወዳዳሪዎች ጋር ብርቱ ፉክክር አድርጋለች ፡፡ በውጤቷም  በ200 ሜትር የወርቅ፣ በ100 ሜትር ደግሞ የብር መዳሊያዎች ተሸላሚ ሆናለች ፡፡

ወጣት ራሄል በትምህርት ቤት ደረጃ ታደርገው የነበረው ጥረት ለአትሌቲክ ስፖርት ጅማሮዋ መነሻ እንደሆናት ተናግራለች ፡፡ ወጣት ራሄል በተለያዩ የአገር ውስጥና የውጭ ውድድሮች አገሯን በመወከል መወዳደሯንና በዚህም የተሻለ ውጤት ማስመዝገቧን ገልጻለች ፡፡ ውድድሮቹ በራስ የመተማመን ብቃት ለመፍጠር እንዳስቻሏትና አሁን ላይ አሉ ከሚባሉ አትሌቶች ተርታ ለመሰለፍ እንዳበቃት ጠቅሳለች ፡፡
በአሁኑ ወቅት በመቻል የአትሌቲክስ ስፖርት ክለብ ውስጥ በቋሚ ተወዳዳሪነት እየሠራች እንደምትገኝ የጠቀሰችው ራሄል አሁን ለደረሰችበት ደረጃ ለመብቃት የቤተሰቦቿ እና የአሠልጣኞቿ ድጋፍ ትልቅ እንደሆነም ተናግራለች  ፡፡ 
ማንኛውም ዓላማ የራሱ ተግዳሮቶች እንዳሉት የጠቀሰችው ራሄል በተለይ በአጭር ርቀት ስፖርት ብዙ ፈተናዎች ያጋጥማሉ ብላለች ፡፡
በቀጣይ የአትሌቲክስ ብቃቷን ከፍ በማድረግ የአገሯን ሥም በዓለም አደባባይ የማስጠራት ግብ እንዳላት ወጣት ራሄል ተናግራለች ፡፡  ወጣት ሴቶች ካሰቡበት ለመድረስ ሁሉንም ነገር በትዕግሥት ከታች መጀመርና በሂደት ሊጋጥሟቸው የሚችሉ ችግሮቹን ለመጋፈጥ መዘጋጀት አለባቸው ትላለች፡፡ #GirlzOffMute  #ዝምታሰባሪአዳጊሴቶች

ዘገባ: ሊሻን ዳኜ
ቪዲዮ: ሸዋንግዛው ወጋየሁ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW