ማስታወቂያ
በዚህ ዓመት በኢትዮጵያ የእንግሊዝ ኤምባሲ እና የብሪቲሽ ካውንስል አንድ የጽሑፍ ውድድር አዘጋጅተው ነበር። በዚህ የሥነ ጽሑፍ ውድድር ከ14 ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ከ300 በላይ ተማሪዎች ያሸንፍልናል ያሉትን ጽሑፍ ለውድድር ይዘው የቀረቡ ሲሆን አዲስ አበባ የሚገኘውና ሴቶች ብቻ የሚማሩበት ናዝሬት ትምህርት ቤት ውስጥ የ11 ክፍል ተማሪ የሆነችው ሩት ሳሙኤል የሴቶች መብትን በሚመለከት ባሰናዳችው ጽሑፍ አሸናፊ ሆናለች።
ታዳጊዋ ይህንን ውድድር በማሸነፏ "Ambassador for a day 2024" በኢትዮጵያ የእንግሊዝ ኤምባሲ የ2024 የአንድ ቀን አምባሳደር የሚለውን ሽልማት ለማግኘት ችላለች።
ይህንን ተከትሎ በBritish Council ውስጥ የሚከናወኑ ሥራዎችን ለመጎብኘት፣ ከእንግሊዝ አምባሳደር በኢትዮጵያ ጋር በኤምባሲው የልምድ ልውውጥ ለማድረግ እንዲሁም ከትውልደ ኢትዮጵያዊው እውቅ ገጣሚ ለምን ሲሳይ ጋር የመወያየት እድል አግኝታለች።
#ዝምታሰባሪአዳጊሴቶች #GirlzOffMute
ዘገባ፡ ሱመያ ሳሙኤል
ቪዲዮ፡ ሰለሞን ሙጬ