1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ኪነ ጥበብኢትዮጵያ

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: ታዳጊዋ ቲክቶከር

03:37

This browser does not support the video element.

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 5 2017

“ የቲክቶክ ሥራን ትምህርት ዝግ በነበረበት ወቅት በዕረፍት ጊዜዬ ነበር የጀመርኩት “ ትላለች ታዳጊዋ ቲክቶከር ብሌን ታገል ፡፡ ነዋሪነቷ በደቡብ ኢትዮጲያ ክልል ጌዲኦ ዞን ይርጋጨፌ ከተማ ነው ፡፡ አሁን ላይ ከወንድሟ ጋር በመሆን በምታስተላልፋቸው የቲክቶክ ቪዲዮች ከአንድ ሚሊየን በላይ ተከታዮች ማፍራት ችላለች ፡፡

በአብዛኛው የምታስተላልፋቸው መልዕክቶች በማህበራዊ ጉዳይ ላይ የሚያተኩሩና እያዝናኑ የሚያስተምሩ መሆናቸው የጠቀሰችው ብሌን “ ሰዎች የተለያዩ አስተያየቶችን ይሰጡኛል ፡፡ በተለይ እማማ ዝናሽ የሚባሉ አናትን አስመስዬ ሥለምጫወት ብዙዎች በስሜ ሳይሆን “ እማማ ዝናሽ “  እያሉ ነው የሚጠሩኝ ፡፡ የትምህርት ቤት ጓደኞቼ እና የሰፈር ጎረቤቶች ሥራዎቼ ጥሩ መሆናቸውን በመገልጽ ያበረታቱኛል  “ ብላለች ፡፡
“ ቲክቶክ ለመሥራት የምጠቀመው ጊዜ አነስተኛ መሆኑ በትምህርቴ ላይ ተፅኖ አላሳደረብኝም “ የምትለው ብሌን “ወደፊት ከቲክቶክ ሥራው ጎን ለጎን የህክምና ዶክተር የመሆን ህልም አለኝ ፡፡ በእኔ ዕድሜ የሚገኙ ታዳጊዎች በውስጣቸው ያላቸውን ችሎታ አውጥተው መጠቀም አለባቸው ፡፡ ቤተሰቦቻቸውም ልጆችን መደገፍና ማበረታታት አለባቸው “ ብላለች ፡፡እስካሁን ከዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች ዝግጅት እንግዶች በእድሜ ትንሿ የሆነችው ብሌን ታገል። #ዝምታሰባሪአዳጊሴቶች #GirlzOffMute


ዘገባ: ሊሻን ዳኜ 
ቪዲዮ:ሸዋንግዛው ወጋየሁ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW