1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ሳይንስኢትዮጵያ

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: የፈጠራ ክህሎት ኮከብ

04:16

This browser does not support the video element.

ማክሰኞ፣ ኅዳር 3 2017

አፍራህ ሁሴን ከእህቷ ሱመያ ሁሴን ጋር ሆነው ገና በልጅነታቸው የጀመሩት የፈጠራ ስራ አሁን ላይ አድጎ ተስፋ ሰጪ ደረጃ ደርሷል። እህማማቾቹ O-skills የተሰኘ ቤተሙከራ እና ዎርክሾፕ ያለው የስልጠና ተቋም አዲስ አበባ ላይ ከፍተዋል።

አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ (AI)ን ተጠቅማ የፈጠራ ስራዋን በመከወን ላይ የምትገኘው አፍራህ ለምሳሌ ደረጃዎችን መውጣት የሚችል የአካል ጉዳተኛ ወንበር (ዊልቸር)ከመስራት ጀምሮ የሌሎች የበርካታ ፈጠራዎች ባለቤት ናት፡፡ ማየት ለተሳናቸው የሚረዳ ጽሁፍን ወደ ድምጽ መቀየር የሚችል ማንበቢያም ሰርታለች።

አፍራህ በፈጠራዋ በርካታ አገራዊ እና ዓለማቀፋዊ እውቅናዎችን አግኝታለች።  “AI for good” በተሰኘው የአርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ጉባኤም ለመሳተፍ  ወደ ጄኔቫ እና ሌሎች የውጭ ሀገራት ከተሞች ተጉዛለች።  የ2024 “AI scholar” ለመባልም በቅታለች፡፡ #ዝምታሰባሪአዳጊሴቶች #GirlzOffMute

ዘጋቢ፡ ሱመያ ሣሙኤል

ቪዲዮ፡ ሥዩም ጌቱ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW