ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ሰኞ፣ መስከረም 19 2018ማስታወቂያ
ማስተዋል ከግጥም እና ከዝማሬ ሥራዎቿ በተጨማሪ “ ምክሬን ላካፍላችሁ “ በሚል ርዕስ ለዕድሜ አኩዮቿ የሚውል መጸሀፍ ለህትመት አብቅታለች ፡፡ መጽሀፉ በውስጡ መንፈሳዊና ሥነ ልቦናዊ ይዘቶችን የያዘ ነው ብላለች ፡፡
አሁን ላይ የታዳጊ ማስተዋል ዝማሬዎች በተለያዩ የ ዩ ቲዩብ ቻናሎች ለእይታ የቀረቡ ሲሆን በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እየተመለከቷቸው ይገኛሉ ፡፡ ግጥሞቿን ፣ ድርሰቶቿን እና ዝማሬዎቿን አስመልክቶ ሰዎች በጎ አስተያየቶችን በመስጠት እንደሚያበረታቷት ጠቅሳለች ፡፡
ለአካል ጉዳተኛ መብቶች ለሚሟገቱ የህግ ባለሙያዎች የተለየ አድናቆት እንዳላት ገልጻለች ፡፡አሷም ወደፊት የህግ ባለሙያ የመሆን ፍላጎት እንዳላትና ለዚህም እንደምትጥር ተናግራለች ፡፡ በአካል ጉዳት ውስጥ ለሚገኙ ታናናሾቼ እና ታላላቆቼ መልዕክት አለኝ የምትለው ታዳጊዋ “ ዐይነ ስውራንም ሆንን ሌሎች አካል ጉዳተኞች የማይቻል ምንም ነገር እንደሌለ ማመን አለብን ፡፡ ትልቅ ቦታ ደረሰን ማህበረሰባችንን እና አገራችንን መጥቀም እንችላለን “ ብላለች ፡፡ #ዝምታሰባሪአዳጊሴቶች #GirlzOffMute
ዘገባ: ትንቢት ሰውነት
ቪድዮ: ሸዋንግዛው ወጋየሁ
