ዝግጅት ለአዲሱ የትምሕርት ዘመን
ሐሙስ፣ ነሐሴ 15 2006ማስታወቂያ
ያጋመስነው የነሐሴ ወር ተማሪዎች ና ትምህርት ቤቶች ለአዲሱ የትምህርት ዘመን ዝግጅታቸውን የሚያጠናቅቁበት ወቅት ነው ። ክረምቱን በማጠናከሪያ ትምህርት በንባብ ወይም በእረፍት ያሳለፉ ተማሪዎች ለመጪው የትምህርት ዘመን የሚያስፈልጓቸውን እንደ ደብተር ብዕር መፃህፍትና የመሳሰሉትን በብዛት ሲገዙ የሚታዩት በዚህ ወቅት ላይ ነው ። የትምህርት መሳሪያዎች ገቢያውም በዚህ ወቅት ላይ ነው የሚደራው ።ዝግጅታቸውን ቀደም ብለው የሚያጠናቅቁ ተማሪዎችና ወላጆች መኖራቸውም መዘንጋት የለበትም ። ለመሆኑ ለአዲሱ የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ዝግጅት ምን ይመስላል ? የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚዘብሄር ተማሪዎችንና ወላጆችን አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚዘብሄር
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ