የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ስጋት
ዓርብ፣ ጥቅምት 19 2014
ማስታወቂያ
ከሰሜን የሀገሪቱ አካባቢዎች በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ተመድበው ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎች ከምረቃ በኋላ ወደ አካባቢያቸው ለመሄድ ያለው የሰላም ሁኔታ እንዳሳሰባቸው ገለፁ። ከቤተሰብ ጋር ከተገናኙ መቆየታቸውን እና አሁንም የደስታቸውን ጊዜ ከቤተሰብ ጋር ማሳለፍ ባለመቻላቸው ማዘናቸውን የጠቆሙት ተማሪዎች መንግሥት ለተጋረጠባቸው ስጋት መፍትሄ እንዲያፈልግ ጠይቀዋል። ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎቹ ችግር በሚፈታበት ሁኔታ ላይ ከትምህርት ሚንስቴር ጋር እየተነጋገረ መሆኑን ተናግሯል።
መሳይ ተክሉ
ሸዋዬ ለገሠ
እሸቴ በቀለ