የሀይንሪሽ በል ድርጅት በኢትዮጵያ
ሐሙስ፣ ጥር 13 2002ማስታወቂያ
የአረንጓዴዎቹ ፓርቲ ሀሳብ አመንጪ በሆኑት በታዋቂው ጀርመናዊ ደራሲ Heinrich Böll የተሰየመው ይኽው ድርጅት ከሚንቀሳቀስባቸው አገራት አንዷ ኢትዮጵያ ናት ። በዛሬው አውሮፓ እና ጀርመን ዝግጅታችን የሀይንሪሽ በል ድርጅት በኢትዮጵያ ስለሚያከናውናቸው ተግባራት ሳምንት በይደር ያቆየነው ቀሪ መሳናዶ አለን ።
ጀርመን ውስጥ ከአጠቃላዩ ሰራተኛ በመቶ ሲሰላ እጅግ ጥቂት የሆነውን በአገልግሎት መስጫ ዘርፍ የተሰማራውን የውጭ ዜጋ ቁጥር ከፍ ለማድረግ የቀረበ አንድ አዲስ ሀሳብ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀረ ። በጀርመን የውጭ ዜጎች ከህብረተሰቡ ጋር ተቀራርበው የሚኖሩበትን መንገድ በሚያመቻቸው ኮሚሽን ኮሚሽነር ማርያ ቦህመር Maria Boehmer የቀረበው ይኽው ሀሳብ የጀርመን ፖለቲከኞችን ድጋፍ አላገኘም ።
ሂሩት መለሰ