1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ሕግ እና ፍትሕ

የሁለቱ የዋልድባ ገዳም መነኮሳት የፍርድ ቤት ውሎ

ሰኞ፣ መጋቢት 10 2010

በፀረ ሽብር ሕግ ተከሰው በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የሚገኙ ሁለት የዋልድባ ገዳም መነኮሳት የእምነት ልብሶቻቸውን በግዳጅ እንዲያወልቁ ማረሚያ ቤቱ ያስተላለፈው ትዕዛዝ በፍርድ ቤት ተነሳላቸው።

Äthiopien Journalisten Martin Schibbye und Johan Persson
ምስል፦ AP

በመነኮሳቱ ላይ የተመሰረተው ክስ እንዲቋረጥ ጥያቄ ቀርቧል።

This browser does not support the audio element.

ብይኑን የሰጠው አባ ገብረሥላሤ እና አባ ገብረየሱስ የተባሉት ተከሳሾች ጠበቃ የማረሚያ ቤቱን ርምጃ በመቃወም ያቀረበውን አቤቱታ በዛሬው ዕለት ያዳመጠው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ የወንጀል ችሎት ልደታ ምድብ ነው። ከወትሮዉ በተለየ በዛሬዉ ዕለት የመነኮሳቱን የፍርድ ቤት ዉሎ ለመከታተል ቁጥሩ በርከት ያለ ሕዝብ በስፍራዉ ተገኝቷል። ዛሬ የተሰየሙት አዳዲስ ዳኞች ሲሆኑ ፍርድ ቤቱ በቀጣይ መነኮሳቱ ላይ የአቃቤ ሕግ ምስክሮችን ለመስማት ለመጋቢት 18 ቀን 2010ዓ,ም ቀጠሮ መስጠቱንም ለመረዳት ተችሏል።  

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር

አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW