የሂሮሺማ እና ናጋሳኪ የአቶም ቦምብ ጥቃት 78ኛ ዓመት
ዓርብ፣ ነሐሴ 19 2015
በጃፓን ሂሮሽማ እና ናጋሳኪ ከአቶም ቦምብ ጥቃት 78ኛ ዓመት ከተሞች ላይ የአሜሪካ አዉቶም ቦንቦች የተጣሉበት አሰቃቂ ጥቃት 78 ዓመት ከሁለት ሳምንት በፊት ታስቦ ዉልዋል። ቀኑ በጃፓን ወደ 200 ሺህ በላይ ህዝብ ያለቀበትን እለት ብቻ ሳይሆን ያወሳዉ፤ በተለያዩ ሃገሮች አደባባዮች ላይ የአቶም ጦር መሳርያ አስከፊነትን የሚያንፀባርቁ ሰላማዊ ሰልፎችም ተካሂደዋል። በርግጥ በጃፓኖቹ ሂሮሽማ እና ናጋሳኪ ከተሞች ላይ በደረሰዉ እልቂት ይህን ያህል ሰዉ ተገድሏል ተብሎ በዉል ባይታወቅም፤ ከፍንዳታዉ በኋላ ተርፈዉ በጨረር ተመርዘዉ የሞቱ፤ ከልጅ ልጅ በጨረሩ ተመርዘዉ ለበሽታ የተዳረጉ ጥቂቶች አይደሉም።
ስለማይሽር ጠባሳቸውና ህመማቸው የሚናገሩት የ90 ዓመቷ ሳዳ ካሳኦካ በሂሮሺማ ከተማ በሚገኘዉ የሰላም ሙዚየም ውስጥ መድረክ ላይ ቆመው የችግሩን የእልቂቱን እና የስቃዩን መጠን በቃላት ለመግለፅ ቃላት አጥሯቸዋል፤ ስሜታቸዉንም ተፈታትኖዋቸዋል። በመድረክ ላይ ታሪኩን ለመናገር የድምፅ ማጉያ አልፈለጉም። አዛዉንቷ ጃፓናዊት ድምጼ ጥርት ብሎ የሚሰማ ብሎም ጠንካራ ነዉ፤ ሲሉ ነዉ ምክንያታቸዉን የገለፁት።
ሳዳ ካሳኦካ የዛሬ 78 ዓመት ሐምሌ 30 ቀን 1937 ዓ.ም አሜሪካ በሂሮሽማ ላይ አቶሚክ ቦንብን በጣለችበት ወቅት የ 12 ዓመት ታዳጊ ህጻን ነበሩ። የሄሮሽማን እልቂት መታሰብያ በተዘጋጀ መድረክ ላይ ቆመዉ ስለገጠመኙ ንግግር ሲያደርጉ አንዳንድ ጊዜ ለአጭር ሲኮንዶች እና ደቂቃ በዝምታ ይዋጣሉ፤ ደግሞም ንግግራቸዉን ይቀጥላሉ። ሳዳ ካሳኦካ ሐምሌ 30 ቀን 1937 ዓ.ም እለት ህይወታቸዉ ከመቅስበት በተገለባበጠበት ወቅት ያጋጠማቸዉን፤ ማንም የማይችለዉን ህመም እና ስቃይ ለማስታወስ ዓይኖቸዉን አሁንም ይገጥሙና ዝም ይላሉ፤ ደሞም ይተርካሉ። በአትላንታ ጆርጅያ በሚገኘዉ ሞርሃዉስ ኮሌጅ የታሪክ መምጅር የሆኑት ተባባሪ ፕሮፌሰር ሃይሌ ላሪቦ፤ በሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት ወቅት ጃፓንየሄሮሽማና ናጋሳኪ 75ኛ ዓመት መታሰብያ አይላ ነበር ብለዋል። በርካቶችም በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል።
የ 12 ዓመት ታዳጊዋ የዝያን ጊዜዋ ተማሪ ፤ የዛሬዋ የ 90 ዓመት አዛዉንት ሳዳ ካሳኦካ ሂሮሽማ ከተማ ላይ በደረሰው የኒውክሌር ፍንዳታ ወላጃቸዉን ተነጥቀዋል።
«ፍንዳታው ፤ ተምዘግዛጊ አዉሎ ንፋስ እና ከፍተኛ የዉኃ መጥለቅለቅ ያለበት አንድ ሺህ እጥፍ ከሆነ ሱናሚ ይበልጣል ብዬ ነዉ፤ ብዙ ጊዜ የአደጋዉን ጥልቅ ከባድነት የማነፃፅረዉ »
ሳዳ ካሳኦካ የኒኩሌር ቦምቡ ከወደቀበት ከዋናዉ ቦታ ወደ አራት ኪሎሜትር (3.5 ኪሎ ሜትር ) ርቀት ላይ በሚገኘው መኖርያ ቤት ዉስጥ ስለነበሩ ከቦንቡ የመጀመርያ ጥቃት መትረፋቸዉ እድለኛ ነበሩ።
ይሁንና እየቆየ የ 12 ዓመትዋ ታዳጊ ብቻዋን ተቀምጣ ያለችበት መኖርያ ቤትዋ፤ የወላጆችዋ ቤት፤ መስኮት መፈነዳዳት ጀመረ፤ የወጣትዋ ቆዳ ተገለባበጠ፤ አባትዋ ከፍንዳታዉ በኋላ ቤት ደርሰዉ ስታያቸዉ በፍንዳታዉ ጨረር ፊታቸዉ ተገሽልጧል፣ ልትለያቸዉ አልቻለች። ወላጅ እናቷም ጠዋት ከሄዱበት እስከወድያኛዉ አልተመለሱም። ተባባሪ ፕሮፌሰር ሃይሌ ላሪቦ፤ እንደሚሉት ዘ ፋት ማን ተብሎ የተጠራዉ ሁለተኛዉ ቦንብ ከሦስት ቀናት በኋላ ናጋሳኪ ከተማ ላይ ተጣለ።
ኖሪ ሆሶሚትሱ የ60 ዓመት ጎልማሳ ናቸዉ። የሂሮሽማ ቦምብ ጥቃት ተራፊዎች በሚቀርቡበት መድረክ ላይ እየቀረቡ ታሪክን ይመዘግባሉ፤ የጥቃቱን ተራፊዎች ተሞክሮ ጠይቀዉም ጽሑፎቻቸዉን ለህዝብ ያቀርባሉ። ኖሪ ሆሶሚትሱ ይህን የጻፉትን ታሪክ ለህዝብ ብሎም ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ሲያቀርቡ ዘጠኝ ዓመት ሆንዋቸዋል። ኖሪ የሂሮሽማ አቶም ቦንብ ጥቃት ተራፊዋን የ 90 ዓመት አዛዉንት ሳዳ ካሳኦካን ብዙ ጊዜ አግኝተዋቸዋል።የቡድን 7 ጉባኤ በጃፓን
«በሳዳ ካሳኦካ ስብዕና እና ቃል-እምነት በጣም ተማርኬያለሁ። ለመጀመርያ ጊዜ ሳገኛቸዉ በሁለታችን መካከል የሆነ የሚያስተሳስረን ነገር እንዳለነዉ የተሰማኝ። በሚሰጡት ምስክርነትም በጣም ተነክቻለሁ። ቁጭ ብሎ በመጠበቅ ሰላም አይመጣም እያንዳንዳችን ሰላም የመፍጠር ሃላፊነት አለብን»
በቃለ-መጠይቅ መጨረሻ ቁጭ ብሎ በመጠበቅ ሰላም አይመጣም እያንዳንዳችን ሰላም የመፍጠር ሃላፊነት አለብን፤ ማለትን የሚያዘወትሩት ኖሪ ሆሶሚትሱ፤ ከሂሮሽማ እና ከናጋሳኪ ጥቃት የተረፉ ሰዎች እድሚያቸዉ በአማካኝ 85 በመድረሱ ታሪኩን ለማቆየት እና ለትዉልድ ለማስተላለፍ ይበልጥ መጠየቅ ይበልጥ መመዝገብ አለብን ሲሉ አበክረዉ ይናገራሉ።
በሂሮሺማ የሚገኘዉ የዓለም አቀፉ የሰላም አራማጅ ድርጅት ባልደረባ ዳን ሺዮካ እንዳሉት የሂባኩሻ ማለትም ከሂሮሽማ እና ነጋሳኪ የኒኩሌር ቦንብ ጥቃት የተረፉ ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱን ተናግረዋል።
ኢራን እና የዩኤስ አሜሪካ ፕሬዚደንት ማስጠንቀቂያ«አሜሪካ የዛሬ 78 ዓመት የጣለችዉን ሁለት የኒኩሊየር ቦንብ ጥቃቶችን እና ዉድመቱን በተመለከተ እስካሁን ከ250 በላይ የታሪክ ባለሙያዎች ስልጠና ቢያገኙም ተጨማሪ ይህን አስከፊ ታሪክ የሚናገር ከመጥፋቱ በፊት በአስቸኳይ ሰንዶ ማስተላለፍ ያስፈልጋል"»
በሂሮሽማ ከደረሰዉ አሰቃቂ ጥቃት በኋላ ብዙም ሳይቆይ ከተማዋ የመንገድ ስራን ስትጀምር እና ወደ መልሶ ግንባታ ስትገባ፤ ጎን ለጎን ለሰላም መታገልንም ጀምራለች። እንደ ጎርጎረሳዉያን አቆጣጠር በ 1955 ሂሮሽማ ከተማ የኒውክሌር ጦር መሳሪያዎችን ለማጥፋት የሚታገል የሰላም ከንቲባዎች የመረብ አውታርን አቋቁማለች ። ይህ የሰላም መረብ ዛሬ ከ 8,000 በላይ ማዘጋጃ ቤቶችን በስሩ መማድረግ የአቶም ጦር መሳርያ ከዓለም ላይ እንዲጠፋ በመታገል ላይ ይገኛል። የአቶም ጦር መሳርያን ለማጥፋት የሚታገለዉ ይህ ቡድን ባለፈው ግንቦት ወር ሂሮሺማ ላይ ተሰይመዉ ለነበሩት ለበለፀጉት ሰባት አገራት ማለትም ለቡድን 7 መሪዎች በጻፈዉ ግልጽ ደብዳቤ አቋሙን አስረግጦ አሳዉቀዋል። አውታረ መረቡ በደብዳቤዉ "የኒውክሌር ጦር መሳሪያዎችን መቀነስ ብሎም ገዳዩን ጦር መሳርያ ማዘመን እንዲገታ አፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድ" ሲል ጠይቋል።የመጀመሪያው የአቶም ቦምብ ፍንዳታ
ሂባኩሻ በሚል የሚጠሩት የአቶም ቦንብ ጥቃት ተራፊዎች ለአስርተዓመታት አድሎ እና መገለል ይደርስባቸዉ እንደነበር ተመልክቷል። የ 90 ዓመትዋ አዛዉንት ሳዳ ካሳኦካም ከ 20 ዓመት በፊት ይህንኑ ነዉ የተናገሩት። ከዚህ ጊዜ ወዲም ታሪካቸዉን በአደባባይ ከመናገር ወደ ኋላ ብለዉ አያዉቁም።
«በልጅነቴ, መምህር የመሆን ህልም ነበረኝ። ነገር ግን በአንድ ነጠላ የአቶም ቦምብ፣ ህልሞቼ፣ ተስፋዎቼ፣ የወደፊት እድሌ ሁሉ በኖ ቀረ። አሁን ፤ ዛሬ እኔ ያንን አሳዛኝ ክስተት የማስታወስ እና ዳግም እንደማይከሰት ማረጋገጥ የእኔ ድርሻ ነው ብዬ አስባለሁ»
ሲሉ የ 90 ዓመትዋ አዛዉንት ተናግረዋል። አሰቃቂዉ ታሪክ ለዘላለም ሲነገር እንዲኖር እንደሚፈልጉም ተናግረዋል።እስራኤል እና የአቶም ቦምብ መሳርያ
"ለዘላለም መኖር እፈልጋለሁ፤ ታሪኬም መነገሩ እንዲቀጥል እፈልጋለሁ። ተተኪዎች፤ ታሪክ ጸሐፊዎች ይህን እንዲቻል ያደርጋሉም"
በአውቶም ቦምቡ ጥቃቱ ምክንያት ጃፓን በ1937 እጅ ሰጥታለች። በእስያ የነበረውን የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ክፍል ማብቂያን ያበሰረ ነው የሚሉ እንዳሉ ሁሉ በሃሳቡ የማይስማሙም አሉ። የማይስማሙት ጃፓን እጅ ለመስጠት ዳር ዳር እያለች የነበረች ባለችበት ወቅት ሽንፈቷን ከአውቶሚክ ቦምብ ጥቃቱ ጋር ማያያዝ ትርጉም አልባ ነው ሲሉ አስተያየት ይሰጣሉ። ተባባሪ ፕሮፌሰር ኃይሌ ላሬቦ እንደሚሉት፤ ጉዳዩ በሀገረ አሜሪካም ይነሳል።
አሜሪካ በጃፓን ላይ የአቶም ቦንብ ጥቃት የሰነዘረችበት 78ኛ ዓመትን በማስመልከት ስለ ሂሮሽማና ናጋሳኪ ጥቃት የተቀናበረበትን ዝግጅት የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን እንዲከታተሉ እንጋብዛለን።
አዜብ ታደሰ
ማንተጋፍቶ ስለሺ