የሃይማኖት መሪዎች ጉባኤ በሃዋሳ
ሐሙስ፣ ነሐሴ 23 2011
ማስታወቂያ
በኢትዮጲያ ግጭቶችን በመፍታት ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ለፅንፈኝነት መንስኤ የሆኑ ምክንያቶችን በመመርመር መፍትሄ መስጠት ይገባል ሲሉ ሀዋሳ ላይ የተሰበሰቡ የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች አሳሰቡ።የኢትዮጲያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በግጭት አስተዳደርና አፈታት ላይ ለመወያየት ባዘጋጀው መድረክ ላይ የሃማኖት አባቶቹ ፣ወጣቶች ከአግላይ የፅንፈኛ ብሔርተኝነትና ፣የህዝቦችን ማንነት ይክዳል ካሉት አህዳዊ አስተሳሰብ በመራቅ በምክንያታዊነት ብቻ መመራት ይኖርባቸዋል ሲሉ ተናግረዋል።ጉባኤውን የተከታተለው የሃዋሳው ዘጋቢያችን ሸዋንግዛው ወጋየሁ ዝርዝሩን አዘጋጅቷል።
ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ኂሩት መለሰ
ተስፋለም ወልደየስ