1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የህክምና ባለሞያዎች ስራ ለማቆም ያስቀመጡት ቀነ ገደብ ተጠናቀቀ፤ ከዚያስ?

ሰኞ፣ ግንቦት 4 2017

የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች የደመወዝ፣ ሌሎች ጥቅማጥቅሞች እና የስራ ከባቢ ምቹነትን የጠየቁበት የአንድ ወር የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻቸው ዛሬ እንደሚያበቃ እየገለጹ ነው፡፡ ለ30 ቀናት የቀጠለው የባለሙያዎቹ አቤቱታ በዚህን ወቅት ውስጥ አለን ያሉትን 12 ጥያቄዎች ለጤና ሚኒስቴር እና ለሚመለከታቸው አካላት ማስገባታቸውም ተመላክቷል፡፡

HIV-Aids-Epidemie in Äthiopien
ምስል፦ Seyoum Getu/DW

የህክምና ባለሞያዎች ጥያቄ ቀጥሏል፤ ቀጥሎስ ምን ይጠበቅ ይሆን ?

This browser does not support the audio element.

የቀጠለው የጤና ባለሙያዎች ጥያቄ እና መቋጫው
የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች የደመወዝ፣ ሌሎች ጥቅማጥቅሞች እና የስራ ከባቢ ምቹነትን የጠየቁበት የአንድ ወር የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻቸው ዛሬ እንደሚያበቃ እየገለጹ ነው፡፡
ለ30 ቀናት የቀጠለው የባለሙያዎቹ አቤቱታ በዚህን ወቅት ውስጥ አለን ያሉትን 12 ጥያቄዎች ለጤና ሚኒስቴር እና ለሚመለከታቸው አካላት ማስገባታቸውም ተመላክቷል፡፡
በእነዚህ 30 ቀናት ጥያቄያቸው ካልተመለሰላቸው የስራ ማቆም አድማ ለማድረግም የዛቱት ባለሙያዎቹ በተለያዩ መንገዶች ተጽእኖ በመፍጠር መነጋገሪያ እንደሆኑ ቀጥለዋል፡፡

ዛሬ ጠዋት በአዲስ አበባ በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ውስጥ የሚሰሩ ሀኪሞች ሆስፒታሉ ውስጥ ወደ ስራ ከመግባታቸው በፊት ተሰባስበው ባሰሙት መፈክራቸው ከዚህ በፊት በተከታታይ ስያነሱዋቸው የቆዩትን የደመወዝና ጥቅማጥቅሞች ጥያቄዎቻቸውን አስተጋብተዋል፡፡ በሆስፒታሉ ቅጥር ጊቢ ውስጥ በተደረገው ሰልፍ ላይ ከታድሙት መካከል ለደህንነታው ስባል ስማቸው እንዳይገለጽ ጠይቀው አስተያየታቸውን ለዶቼ ቬለ የሰጡ የሰልፉ ተሳታፊ፤ “ብዙ ጥያቄ ስላለን እነዚያን ዘርዝረን ለጤና ሚኒስቴር አስገብተናል” በማለት ከነዚህ ጥያቄዎች የደመወዝ፣ የጤና ኢንሹራንስን ጨምሮ የተለያዩ ጥቅማጥቅሞች እንደሚገኙ በማስረዳት በዛሬ ጠዋቱ የጥቁር አንባሳ ሆስፒታል የመፈክር ማሰሚያ ወቅትም እነዚህን ጥያቄዎቻቸውን ማስተጋባታቸውን አስረድተዋል፡፡ የሀኪሞቹ ጥያቄ በምንም መልኩ ከፖለቲካ ጋር የማይገኛኝ የኑሮ ጉዳይ ነው ያሉት ባለሙያዋ በዛሬ ጠዋቱ የሀኪሞቹ የመፈክር ማሰሚያ ሰልፍ ወቅት ሲቪል በለበሱ ግለሰቦች ወደ ስራቸው እንዲገቡ መደረጋቸውን ጠቁመዋል፡፡

የጤና ባለሙያዎች የመጨረሻ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻና የስራ ማቆም አድማ ማስጠንቀቂያ
ቀጣዩ እርምጃስ..
30 ቃናትን ሲቆጥሩ የቆዩት ሀኪሞቹ በዘመቻቸው መሰረት በቀጣይ በተለይም ከነገ ጀምሮ ለመውሰድ ያቀዱት እርምጃ ምን ይሆን በሚል ጥያቄ የቀረበላቸው የዘመቻው ተሳታፊ ሀኪም ስራቸውን በአንዴ ማቆም አስቸጋሪ በመሆኑ በሂደት ነገሮችን ማጠን አስፈላጊ ሆኖ ማግኘታቸውን እንደመከሩ ነው ያስታወቁትም፡፡ “በአንዴ ለቀን አንወጣም ግን ያው አንድ ብዙ ሰው በሚፈልጉ ቦታዎች ጭምር አንድ ሰው እየመደብን በዙር በመስራት ጫና ማድረጉን መቀጠል ነው ለጊዜው ያሰብነው” ያሉት ባለሙዋ እስካሁን ለጥያቄዎቻቸው የተሰጠ አመርቂ ያሉት ምላሽ አለመኖሩንና ልቁን ጥያቄውን ስተጋቡ ሀኪሞች እየታሰሩ መሆኑን መስማታቸውን ገልጸዋል፡፡

ዛሬ በሚጠናቀቀው የጤና ባለሙያዎች የደመወዝና ሌሎች ጥቅማጥቅሞች ዘመቻ ማብቂያን አስመልክቶ ጤና ባለሙያዎችን የማወያየት ስራዎች ከታች ከወረዳ ጀምሮ በስፋት እየተከናወነ ነው ብለዋልምስል፦ Seyoum Getu/DW

የጤና ባለሙያዎች የደመወዝና የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ
ሀኪሞችን የማወያየት እና ጥያቄዎቻቸውን የማሰባሰብ ዘመቻ
ሌላም አስተያየት ሰጪ ሀኪም ዛሬ በሚጠናቀቀው የጤና ባለሙያዎች የደመወዝና ሌሎች ጥቅማጥቅሞች ዘመቻ ማብቂያን አስመልክቶ ጤና ባለሙያዎችን የማወያየት ስራዎች ከታች ከወረዳ ጀምሮ በስፋት እየተከናወነ ነው ብለዋል፡፡ “እኛ ጥያቄያችንን ለጤና ሚኒስቴር አስገብተናል” ያሉት ባለሙያው የመንግስት አካላት የጤና ባለሙያዎችን አነጋግራችሁ በየደረጃው ላለው መዋቅር አስተላልፉ በሚል እየተንቀሳቀሱ ነው ብለዋል፡፡ ከዚህ በፊት ከነበረው አዲስ ነገር የለውም በማለትም አዲስ የእናወያያችሁ ጥያቄው ላይ ያላቸው ተስፋ አናሳ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ጥያቄያቸውም ግልጽ የመኖር ጥያቄ እንጂ ምንም አይነት ከፖለቲካ ጋር ልያያዝ የሚገባው አይደለም ሲሉ አመልክተዋል፡፡  

የቀጠለው የሕክምና ባለሙያዎች ተቃውሞ
ዶይቼ ቬለ በጉዳዩ ላይ በጤና ሚኒስቴር በኩል አስተያየት ለመጠየቅ ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሕዝብ ግንኙነትና ጤና ኮሚኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ተገኔ ረጋሳ (ዶ/ር) በመደወልና የጽሁፍ መልእክት በመላክ ጥያቄውን ብያቀርብም ምላሻቸውን አላገኘንም። 
የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ኃላፊው ከዚህ በፊት ለዶይቼ ቬሌ እና ሌሎች መገናኛ ብዙሃን በሰጡት ምላሽ ግን በጤና ባለሙያዎችና በሠራተኞች የሚነሱ ጥያቄዎች ተገቢና ዕውቅና የሚሰጣቸው መሆኑን አመልክተው፤ ለዚህም የመካከለኛ የረጅም ጊዜ ዕቅድ ተይዞ መፍትሔ እየተፈለገለት ይገኛል ማለታቸው አይዘነጋም፡፡


ሥዩም ጌቱ
ታምራት ዲንሳ 
እሸቴ በቀለ
 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW