1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የህክም እና የምግብ እትርቦት ችግር በሐይቅ የተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያ

ዓርብ፣ ነሐሴ 17 2016

ደቡብ ወሎ ዞን ተሁለደሬ ወረዳ ሀይቅ ከተማ በሚገኘውና በተለምዶ«ቱርክ» እየተባለ በሚጠራው መጠለያ ጣቢያ የሚገኘኙ ተፈናቃዮች «ወደ መጠለያው የሚያስገባ መንገድ ተበላሽቷል» በሚል የህክምና ባለሙያዎች መምጣት ባለመቻላቸው የህክምና አገልግሎት ማግኘት አልቻልንም ብለዋል። ከህክምና በተጨማሪ በምግብ እትርቦት ችግር መጎዳታቸውን ተፈናቃዮቹ ተናግረዋል።

 በሀይቅ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ተፈናቃዮች
በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን በሀይቅ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ተፈናቃዮች ምስል Alemnew Mekonen/DW

የህክም እና የምግብ እትርቦት ችግር በሐይቅ የተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያ

This browser does not support the audio element.


በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ተሁለደሬ ወረዳ  ሀይቅ ከተማ በሚገኘውና በተለምዶ “ቱርክ” እየተባለ በሚጠራው የተፈናቃዮች  የመጠለያ ጣቢያ የሚገኘኙ ተፈናቃዮች “ወደ መጠለያው የሚያስገባ መንገድ ተበላሽቷል” በሚል የህክምና ባለሙያዎች መምጣት ባለመቻላቸው የህክምና አገልግሎት ማግኘት አልቻልንም አሉ፡፡ የዞኑ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት በበኩሉ በመንገድ መበላሸት ምክንያት ህክምና ስለመቋረጡ የደረሰው መረጃ እንደሌለ አመልክቷል፡፡

ተገቢውን ህክምና የማግኘት  ችግር

ተፈናቃዮቹ ዛሬ ለዶይቼ ቬሌ በሰጡት አስተያየት ወደ መጠለያ ጣቢያው የሚወስደው መንገድ ብልሽት አጋጥሞታል በሚል  ወደ ጣቢያው እየመጡ የህክምና አገልግሎት ይሰጡ የነበሩ ባለሙያዎች መምጣት ካቆሙ ከሳምንት በላይ በመሆኑ ታማሚዎች ተገቢውን ህክምና ማግኘት አልቻሉም፣ በግል ወደ ሌሎች ህክምና ጣቢያ ለመሄድ ቢሞከሩም የህክምና ገንዘብ ማግኘት እንዳልቻሉ ነው የሚገልፁት፡፡ አስተያየት ከሰጡን ተፈናቃዮች መካከል አንዱ እንዳሉት በመጠለያው ጠቅማጥና ትውከት በአንዳንድ ተፈናቃዮች ላ ታይቷል ብለዋል፡፡ ታማሚዎችን በእንጨት አልጋ ተሸክሞ ወደ ሐይቅ ከተማ ህክምና ለማድረግ ቢሞከርም መታከሚያ ገንዝብ ባለመኖሩ ታማሚዎቹ በየጤና ተቋማት በረንዳ ላይ ናቸው ሲሉ አብራርተዋል፣ ብዙ የተመሙና የተዳከሙ ህፃናትና አዛውንቶች መኖራቸውንም አስረድተዋል፡፡

ከህክምና አገልግሎት ችግር ባሻገር ተፈናቃዮቹ በቂ ምግብ እያገኙ እንዳልሆነም ገልፀዋል።ምስል Alemnew Mekonen/DW

በቂ ምግብ ያለማግኘት ችግር

በምግብም በኩል በቂ ምግብ እያገኙ እንዳልሆነም እኚሁ ተፈናቃይ አመልክተዋል፡፡ በመጠለያ ጣቢያው ርሀብ መኖሩን የሚገልፁት እኝህ አስተያየት ሰጪ በቅርቡ የተወሰነ ዱቄት ቢመጣም ዘይትና ጨው የመሳሰሉ ማጣፈጫዎች ባለመምጣታቸው ለመመገብ እንደተቸገሩ ነው የገለጡት፡፡
ሌላ በመጠለያ ጣቢያው የሚገኙ እናት በመጠለያው ከሚገኙ ተፈናቃዮች መካከል ብዙዎቹ ለተቅማጥና ለመተንፈሻ አካል ችግር መዳረጋቸውን ተናግረዋል፡፡ በመንገድ ብለሽት ምክንት የህክምና ባለሙያዎች መምጣት ካቆሙ አንድ ሳምንት ማለፉንም ገልጠዋል፡፡
“ህመምም በርትቶብናል፣ ለህፃናትና ለአቅመ ደካሞች የማይቻል በሽታ ነው” ሲሉ ነው ያለውን ችግር ያስረዱት፡፡

ከህክምና አገልግሎት ችግር ባሻገር ተፈናቃዮቹ በቂ ምግብ እያገኙ እንዳልሆነም ገልፀዋል።ምስል Alemnew Mekonen/DW

የተፈናቃዮቼ በተለያዩ በሽታዎች መጠቃት

በዚሁ መጠለያ ጣቢያ የሚገኝ ሌላ አስተያየት ሰጪ በበኩሉ  ህክምና በመቋረጡ ተፈናቃዮች ረጅም የእግር መንገድ በመጓዝ በግል የህክምና ተቋማት አገልግሎት እያገኙ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡ በዋናነትም በመጠለያ ታጣቢያው ሳል፣ ተቅማጥና የመሳሰሉ በሽታዎች ታይተዋል ነው ያለው፡፡
ጉዳዩን አስመልክተው አስተያየት የሰጡን የደቡብ ወሎ ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽ/ቤት የቅድመ ማስጠንቀቂና ምልሽ ቡድን መሪ አቶ መሐመድ ሰኢድ መንገድ ስለመበላሸቱ ሪፖርት እንዳልደረሳቸው አመልክተው ምናልባት ከወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ አንፃር መንገድ ተዘግቶ ሊሆን እንደሚችል አስረድተዋል፡፡ሆኖም ፀጥታው ሲሻሻል የህክምና አገልግሎቱ እንደሚሰጥ ነው የተናገሩት፡፡
የምግብና የሌሎች አገልግሎቶች እጥረቶችን በተመለከተ ደግሞ አቅም በፈቀደ መጠን እርዳታ እቀረበላቸው እንደሆነ ነው አቶ መሐመድ የገለጡት፡፡
በመጠለያ ጣቢያው አገልግሎት ይሰጥ የነበረውና IOM የተባለ ድርጅት አንድ የህክምና ባለሙያ ሰሞኑን በፀጥታ ምክንያት መንገዶች ዝግ ስለነበሩ ከአካባቢው መውጣታቸውን ተቁመው አሁን ግን የህክምና አገልግሎት ለመስጠት እየተዘጋጁ እንደሆነ ለዶቼ ቬሌ አመልክተዋል፡፡

 

ሙሉ ዝግጅቱን የድምፅ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ,
ዓለምነው መኮንን
ዮሀንስ ገብረ እግዚያብሄር
ፀሀይ ጫኔ

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW