1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የህወሃት ሊቀመንበር መግለጫ

ሰኞ፣ ኅዳር 6 2014

ሊቀመንበሩ በሰጡት መግለጫ፥ የትግራይ ኃይሎች ወታደራዊ ይሁን ሌላ እንቅስቃሴ የመጨረሻ ግብ፥ በትግራይ ላይ ወንጀል የፈፀሙት አካላትን ለፍርድ ማቅረብ፣ ለደረሰው ውድመት ካሣ መጠየቅ እንዲሁም የትግራይ ህዝብ መፃኢ ዕድል ህዝበ ውሳኔ እንዲወስን ማድረግ መሆኑ ተናግረዋል።

Äthiopien Konflikt in Tigray | Debretsion Gebremichael
ምስል Tiksa Negeri/REUTERS

የህወሃት ሊቀመንበር መግለጫ

This browser does not support the audio element.

ህወሓት በኢትዮጵያ ፖለቲካ የ1983 ዓ.ም ዓይነት ሚና ሊኖረው እንደማይፈልግ አስታወቀ። የህወሓት ሊቀ መንበርና በህወሓት የሚመራው የትግራይ ክልል መንግሥት ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረ ፅዮን ገብረ ሚካኤል ትናንት በሰጡት መግለጫ፥ የትግራይ ኃይሎች ወታደራዊ ይሁን ሌላ እንቅስቃሴ የመጨረሻ ግብ፥ በትግራይ ላይ ወንጀል የፈፀሙት አካላትን ለፍርድ ማቅረብ፣ ለደረሰው ውድመት ካሣ መጠየቅ እንዲሁም የትግራይ ህዝብ መፃኢ ዕድል ህዝበ ውሳኔ እንዲወስን ማድረግ መሆኑ ተናግረዋል። የወቅቱ የኢትዮጵያ መንግሥት «በውድቀቱ ዋዜማ» ላይ ነው ያሉት ዶክተር ደብረ ጽዮን፣ «የኢትዮጵያን መንግሥት ለመጣል እና ቀጥሎ ያለውን የሽግግር ሁኔታ ለማመቻቸት» ህወሓትን ጨምሮ ዘጠኝ የፖለቲካ ድርጅቶችን የያዘ ግንባር ተመስርቶ እየተሠሰራ ነው መሆኑንም ገልጸዋል።

 ሚሊየን ኃይለ ሥላሴ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW