1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በህወሓት መግለጫ ላይ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አስተያየት

ማክሰኞ፣ መስከረም 3 2015

ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ህወሀት፣ የሰሜን ኢትዮጵያውን ጦርነት በሰላማዊ መንገድ ለማቆም በአፍሪካ ሕብረት መሪነት በታሰበው የሰላም ሂደት፣ ለመሳተፍ ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ህወሀት፣ በሰላማዊ መንገድ ለማቆም በአፍሪካ ሕብረት መሪነት በታሰበው የሰላም ሂደት፣ ለመሳተፍ እና ተደራዳሪ ቡድን መሰየሙን ከቀናት በፊት አሳውቋል።

Infografik Karte Äthiopien AM

የህወሓት መግለጫና የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አስተያየት

This browser does not support the audio element.

ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ህወሀት፣ የሰሜን ኢትዮጵያውን ጦርነት በሰላማዊ መንገድ ለማቆም  በአፍሪካ ሕብረት መሪነት በታሰበው የሰላም ሂደት፣ ለመሳተፍ  መዘጋጀቱን እና ተደራዳሪ ቡድን መሰየሙን ከቀናት በፊት አሳውቃል። በዛሬው እለት «ቢቢሲ  ሞኒተሪንግ» ባወጣው ዜና ህወሓት ከድርድር በፊት በትግራይ መሰረታዊ አገልግሎቶች  እንዲጀምሩ መጠየቁን አስነብቧል። ከዚህ ቀደም የኢትዩጵያ መንግስት ድርድሩ በአፍሪካ ሕብረት መሪነት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲደረግ ጥሪ ቢያቀርብም (ህውሀት )አደራዳሪው እንዲቀየር እና ከድርድሩ በፊት ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጦ ነበር።ይሁንና የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት  ባለፈው እሁድ ባወጣው መግለጫ ተኩስ ለማቆምና በአፍሪቃ ኅብረት በሚመራው የሰላም ሂደት ለመሳተፍ ዝግጁ ነኝ ብሏል።በህወሓት  መግለጫ ላይ ምን አስተያየት አላችሁ ስንል የተለያዩ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ጠይቀናል። የተቃዋሚው « አረና ትግራይ ለዲሞክራሲያዊና ሉአላዊነት ፓርቲ» ሊቀመንበር አቶ ጎይቶም ፀጋዬ ለፖለቲካዊ ችግር ፖለቲካዊ መፍትሄ እንጂ፣ ጦርነት መፍትሄ ሊሆን አይገባም ይላሉ «ጦርነት ከመጀመሩ በፊትም ጦርነት ከተጀመረም በውሀላም ያለን አቅዋም ፖለቲካዊ የሆነ ችግር መፈታት ያለበት በፖለቲካዊ መንገድ ነው እንጂ በጦርነት አይደለም» ብለዋል ህውሀት ያወጣው መግለጫን ማየታቸውን የተናገሩት አቶጎይቶም «የፌደራል መንግስት ምላሹን አላየሁም አልሰማሁም ነበር   ሆኖም በተግባር መቀሌን በአየር  በመደብደብ ምላሽ ሰጥትዋል  ብለዋል። 

ምስል፦ DW/M. Haileselassie

የአፋር ህዝብ ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ እስማየል ሳህለስ እናደርጋለን የሚሉት ድርድር እውነት አይመስለኝም ብልዋል«በሁለቱም አካል ለድርድር የተዘጋጀ አካል ያለ አይመስለኝም  ህዝቡ ግን በጣም እየተጎዳ ነው እኛ ሰላም እንዲወርድ እንፈልጋለን» ሲሉ አክለውም እኛ ይሄ ድርድር ለማዘናጋት ይመስለኛል  እኛ ሁኔታው በድርድር እንዲያልቅ ነው የፈለግነው ብለዋል

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አብን ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ  አቶ ጣሂር መሀመድ በበኩላቸው  ምንም ድርድር  አያስፈልግም «ህውሀት አገር እንድትፈርስና በኢትዩጵያ ፍርስራሽ ላይ ደሞ ታላቅዋን ትግራይ ለመመስረት የሚያደርገው እንቅስቃሴ ነው  በአፋር  እና በአማራ ህዝብ ላይ ከፍተና ግፍ እየፈጸመነው ያለው ሲሉ ህዝባችንን እና አገራችንን ፈተና ላይ ሊጥሉ አይገባም» ብለዋል  የኢትዩጵያ ዜጎች ማህበር ሊቀመንበር ዶ/ር ጫኔ ከበደ በበኩላቸው ህወሀት ድርድር የሚያውቅ መንግስት አይደለም ይላሉ « አጣብቂን ውስጥ ሲገባ ነው ድርድር ያለው ባለፉት ግዜያት እንኩዋን የተለያዩ መግለጫዎችን ሲሰጥ ነው የቆየው መከላከያ ሰራዊት ትግራይ ክልል ውስጥ አንዳንድ ቦታዎችን በማስለቀቁ ና አጣብቂኝ ውስጥ በማስገባቱ ማሸነፍ እንደማይቻል ሲያውቁት ነው የድርድር ሀሳብ ይዘው የቀረቡት» ብለዋል አክለውም  ህወሀት ወደ ድርድር መጥቶ ሰላም ያመጣል የሚል እምነት የለንም ሲሉ በተደጋጋሚ መግለጫዎችን መስጠታቸው ያነሱት ዶ/ር ጫኔ ህውሀት በጦርነት ነው መሸነፍ ያለበት የሚል አቅዋም እንዳላቸው ገልጸው«ወደ መድረክ መቶ መደራደር የሚችል ከሆነ ምንም ቢሆን አንድ እድል ቢሰጠው የተሻለይሆናል የሚል እንደፓርቲ አቅዋም አለን»  ብለዋል 

ዶቼቬለ የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ከፍተኛ አመራሮችን አስተያየትም ጠይቆ ነበር።ሆኖም አስተያየታቸውን ከመስጠት ተቆጥበዋል። ህወሓት በአፍሪካ ሕብረት የሰላም ድርድር ማዕቀፍ ውስጥ ለመግባት ዝግጁ ነኝ ካለ በኋላ የተመድ የአፍሪቃ ኅብረት ፣የአውሮጳ ኅብረትና በአጠቃላይ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እርምጃውን የሚበረታታ ብሎታል።

ማኅሌት ፋሲል 

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW