1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ህወሓት አዲስ ፕረዚደንት እንዲሰየም መጠየቁን

ሰኞ፣ መስከረም 27 2017

ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በሊቀመንበርነት የሚመሩት የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ቡድን ዛሬ እንዳስታወቀው መስከረም 24 ቀን 2017 ዓመተምህረት ባደረገው የማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ህወሓትን ወክለው በትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ያሉ ባለስልጣናት ከሓላፊነታቸው እንዲወርዱ መወሰኑ ይፋ አድርጓል።

Äthiopien I 14. Kongress der TPLF in Mekelle
ምስል Million Haileslasse/DW

ህወሓት አዲስ ፕረዚደንት እንዲሰየም መጠየቁን

This browser does not support the audio element.

በዶክተር ደብረፅዮን የሚመራው ህወሓት አቶ ጌታቸው ረዳ ጨምሮ 13 የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ባለስልጣናት ከስልጣናቸው እንዲወርዱ መወሰኑ አስታወቀ። በቅርቡ ጉባኤ ያደረገው ይህ የህወሓት ቡድን በምትካቸው የሚሰሩ ያላቸው ሹመቶችም ሰጥቷል። 

ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በሊቀመንበርነት የሚመሩት የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ቡድን ዛሬ እንዳስታወቀው መስከረም 24 ቀን 2017 ዓመተምህረት ባደረገው የማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ህወሓትን ወክለው በትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ያሉ ባለስልጣናት ከሓላፊነታቸው እንዲወርዱ መወሰኑ ይፋ አድርጓል።

የህወሓት ጉባኤ ዳግም ጦር ያማዝዝ ይሁን?

በግዚያዊ አስተዳደሩ ሃምሳ ሲደመር አንድ ድርሻ እንዳለው የገለፀው የህወሓት ቡድኑ፥ ህወሓትን ወክለው በግዚያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ፣ የዞን አስተዳደር እና ኤጀንሲዎችና ኮምሽኖች ያሉ ባለስልጣናት መቀየሩ አስታውቋል።

በዚህ መሰረት የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ "ግዚያዊ አስተዳደሩ ሊመሩ በህወሓት የተሰጣቸው መነሳታቸው፥ እንዴት እና በማን ይተካሉ የሚል ደግሞ ከፌደራል መንግስቱ እና የሚመለከታቸው አካላት በመግባባት ይፈፀማል" ሲል ዛሬ ባወጣው መግለጫው ይፋ አድርጓል።

የቀጠለዉ የትግራይ ፖለቲከኞች ዉዝግብ

ከዚህ በተጨማሪ አቶ በየነ ምክሩ፣ ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረህይወት፣ ዶክተር ሓጎስ ጎደፋይ ጨምሮ ሌሎች በህወሓት ውክልና ወደ ግዚያዊ አስተዳደሩ የገቡ ባለስልጣናት ማውረዱ የገለፀው የፓርቲው መግለጫ በምትካቸው ደግሞ እነ ዶክተር አብርሃም፣ አቶ አማኑኤል አሰፋ፣ ዶክተር ፍስሃ ሃፍተፅዮን ሌሎች ለተለያዩ ሐላፋነቶች መሾሙ ያትታል።

የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሓኖም የትግራይ ፖለቲከኞች ችግሮቻቸው በሰላም እንዲፈቱ ጥሪ አቀረቡ

በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመሩ የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ አባላት እና ሌሎች በቅርቡ አካሂደውት በነበረ "ህወሓት ማዳን" የተሰኘ ስብሰባ፥ ጉባኤ ያደረገው ህወሓት በሕገወጥነት ፈርጀው በቅርቡ ሌላ ጉባኤ እንደሚያደርጉ ገልፀው እንደነበረ ይታወሳል። 
ሚልዮን ሃይለስላሴ
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር
ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW