1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የህወሓት ኃይል ከአማራና ከአፋር ክልሎች እንዲወጣ ተጠየቀ 

ረቡዕ፣ ሐምሌ 28 2013

ተፋላሚ ኃይሎች በድርድር ላይ የተመሰረተ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመድረሰ መነጋገር እንዲጀምሩም ጥሪ ቀርቦላቸዋል።

USA Ned Price Sprecher State Department
ምስል Alex Brandon/AP/picture alliance

የህወሓት ኃይል ከአማራና ከአፋር ክልሎች እንዲወጣ ተጠየቀ 

This browser does not support the audio element.

 

ዮናይትድስቴትስ ፣ ህወሓት ወታደራዊ ኃይሉን ከአማራና አፋር ክሌሎች በአስቸኳይ እንዲያስወጣ ጠየቀች። የአሜሪካ  ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ ኔድ ኘራይስ ትናንት ለጋዜጠኛ በሰጡት መግለጫ የአማራ ክልላዊ መንግስትም ወታደራዊ ኃይሉን ከምዕራባዊ ትግራይ እንዲያስወጣ በድጋሚ ጥሪ እናቀርባለን ብለዋል።በሰሜን ኢትዮጵያ ተስፋፍቶ የቀጠለው ውጊያ እንዳሳሰባቸው ገየገለጹት ፕራይስ የኤርትራ መንግስትም ወታደራዊ ኃይሉን ከኢትዮጵያ በዘላቂነት እንዲያስወጣ በድጋሚ ጠይቀዋል። ተፋላሚ ኃይሎች በድርድር ላይ የተመሰረተ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመድረሰ መነጋገር እንዲጀምሩም አሳስበዋል።ከአትላንታ ጆርጅያ ወኪላችን ታሪኩ ኃይሉ ተጨማሪ ዘገባ ልኮልናል ። 
ታሪኩ ኃይሉ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW