«የህወሓት አመራሮች ትግራይን ወደሌላ ጥፋት ከሚያስገባ አካሄድ ይቆጠቡ» ሳልሳይ ወያነ ትግራይ
ማክሰኞ፣ ግንቦት 26 2017
«የህወሓት አመራሮች ትግራይን ወደሌላ ጥፋት ከሚያስገባ አካሄድ ይቆጠቡ» ሳልሳይ ወያነ ትግራይ
የህወሓት አመራሮች ካለፈ ጦርነት ያላገገመች ትግራይ ዳግም ወደሌላ ጥፋት ከሚያስገባ አካሄድ ይቆጠቡ ሲል ተቃዋሚው ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ገለፀ። በሌላ በኩል በክልሉ ተደቅኖ ያለ ፖለቲካዊ እና የፀጥታ አደጋ የሚያስቀር እውነተኛ ፖለቲካዊ ውይይት እንዲደረግ ፓርቲው ጥሪ አቅርቧል። ሳልሳይ ወያነ ትግራይ የህወሓት ወታደራዊ ክንፍን መክሰሱ
በትግራይ በተቃዋሚነት የሚንቀሳቀሰው ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ትላንት ባሰራጨው መግለጫ እንዳለው ከኢትዮጵያና ኤርትራ መንግስታት ባህሪ እንዲሁም እያካሄዱት ካለ የሚድያ ዘመቻ በመነሳት ሲታይ ወደ ጦርነት እያመሩ መሆኑ መረዳት ይቻላል ያለ ሲሆን፥ እነዚህ በጋራ በትግራይ ላይ ጦርነት ከፍተው የነበሩ ሐይሎች ዳግም ትግራይ የጦርነት አውድማ እንዳያደርጓት ስጋቱ ከፍተኛ መሆኑ አመልክቷል።
የትግራይ ጉዳይ አጀንዳዎች ያለሆኑ የህወሓት መሪዎች፣ ትግራይ ካለፈው ጦርነት ጠባሳ ሳታገግም ወደ ሌላ ጦርነት የምትገባበት ፖለቲካዊ አካሄድ ከጀመሩ ቆይተዋል በማለት የከሰሰው ሳልሳይ ወያነ ትግራይ፥ በተለያየ አቅጣጫ ተሰልፈው ትግራይን ወደጦርነት እየገፉ ያሉ ቡድኖች ከድርጊታቸው ይቆጠቡ ብሏል። ለዶቼቬለ የተናገሩት የሳልሳይ ወያነ ትግራይ ሊቀመንበር አቶ አሉላ ሃይሉ የትግራይ ፖለቲከኞች ህዝቡን ለአደጋ የሚያጋልጥ አካሄድ ያቁሙ ብለዋል።"ወደ ሥርዓት አልበኝነት ሊያመራ ይችላል"
በሌላ በኩል ሳልሳይ ወያነ ትግራይ እንዳለው፥ አላማቸው እና ጥያቄዎቻቸው በሰላማዊ እና ሕጋዊ መንገድ እንዳያስፈፅሙ የተገፉ የትግራይ ልጆች አፈሙዝ ለማንሳት ተገደዋል ያለ ሲሆን፥ ይህ እንዲፈጠር ያደረገ ሁኔታ የሚቀይር እውነተኛ ፖለቲካዊ ውይይት በማድረግ ተደቅኖ ያለው የከፋ አደጋ እንዲቀለበስ እንዲሰራ ጥሪ አቅርቧል።
በትግራይ ያለው ፖለቲካዊ ሐይል የተቃወሙ ታጣቂዎች ማእከላቸው ዓፋር ክልል አደርገው እየተንቀሳቀሱ መሆኑ መረጃዎች ያመለክታሉ።
ሚሊዮን ኃይለሥላሴ
አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ