1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የህወሓት ጉባኤ እና የህጋዊነት ጥያቄ ላይ የህግ ባለሙያ ምልከታ

ረቡዕ፣ ነሐሴ 8 2016

ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) እያካሄደ ያለው ጉባኤ የህግ ጥያቄ የሚነሳበት መሆኑን የህግ ባለሙያ አመለከቱ፡፡ ይህም ህወሓት መካከል ከተፈጠረው አለመግባባት ጋር ተዳምሮ ፓርቲውን ዳግም ከማዕከላዊ መንግስት ጋር የከረረ ውዝግብ ውስጥ ሊያስገባው እንደሚችል ይጠቁማሉ፡፡

የህወሓት ጉባኤ
የህወሓት ጉባኤምስል Million Haileselassie/DW

የህግ ባለሙያ ምልከታ

This browser does not support the audio element.

በማናቸውም ፍርድ ቤት ጠበቃ እና የህግ አማካሪው የህግ ባለሙያ አንዱኣለም በእውቀቱ እንደምሉት ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) አሁን እያደረገ ያለው ጠቅላላ ጉባኤ የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት መከሰትን ተከትሎ የተሰረዘውን የፓርቲውን ህጋዊነት ለመመለስ የተደከመበትን ልፋት መና የሚስቀር ነው፡፡ የፌዴራሉ መንግስት ህወሓትን ዳግም በህጋዊነት ለማስመዝገብ የአዋጅ ማሻሻያ እስከማድረግ ብደርስም ህወሓት እያከናወነ ያለው ጠቅላላ ጉባኤ በምርጫ ቦርድ ቅቡልነት ሊኖረው የማይችልበትንም ምክንያት አብራርተዋል፡፡ 

የተፈጠረውን የህግ ክፍተት ለመሙላት የወጣው አዋጅ ፋይዳ

“የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ የምርጫ ስነምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 በአመጽና በኃይል የተሰማራን የፖለቲካ ድርጅት ፍቃድ ይሰርዛል፡፡ ዳግም እንዳይመዘገብም ከለክላል፡፡ ቦርድ የፓርቲውን ዳግም ምዝገባ ስቃወም የነበረውም እንደዚህ አይነት የህግ ክፍተት ስለሌለ ነው፡፡ ያንን ተከትሎ ህወሓት አንጋፋ ድርጅት እንደመሆኑ በዚያው ስሙ ወደ ህጋዊነት ለመመለስ በመፈለጉ ከማዕከላዊ መንግስት ጋር ስደራደር ነበር፡፡ አዋጅ ቁጥር 1332/2016 በሚል እስከማውጣትም የደረሰው ፌዴራል መንግስት ህወሓት ከዚህ በፊት የተሰማራበትን የአመጽ ተግባር በፕሪቶሪያው ስምምነት በመግታቱ አሁን በህጋዊነት ብመዘገብ ቅሬታ የለንም የሚል መልእክት በማስተላለፍ ነው” ሲሉም ሃሳባቸውን አብራርተዋል፡፡


ህወሓት ተመዝግቦበታል ያሉትንም ልዩ ሁኔታ ያብራሩት የህግ ባለሙያው ለህወሓት በተሰጠው የህጋዊነት ሰርቲፊኬት ላይ ፓርቲው በልዩ ሁኔታ መመዝገቡን እንደምጠቅስ በመጠቆም፤ ይህም በፕሪቶሪያ በተፈረመው ስምምነት መሰረት ሰላምን ለማጽናትና የስምምነቱን ጭብጥ ጉዳዮች መሬት ላይ ለመተግበር ታስቦ መሰራቱን የሚያሳይ ብለውታል፡፡ የህግ ባለሙያው ይህ በአዋጅ ተደገፈው የህግ ማሻሻያ ህወሓትን ታሳበቪ አድርጎ ይውጣ እንጂ ከዓመጽ ተግባር ለመመለስ የፈለጉትን ሁሉንም አካላት ሚጠቅም ብለውታልም፡፡የሰሞኑ የህወሐት ስብሰባና የተቃዋሚዎች አስተያየት

የህወሓት ጠቅላላ ጉባኤ ምስል Million Haileselassie/DW

ሊጠበቅ ስለሚችለው የድህረ ጉባኤው ውሳኔ

ከፕሪቶሪያው ስምምነት በፊት ህወሓት በሽብርተኝነት ተፈርጆ እንደነበር ያስታወሱት ጠበቃ አንዱኣለም፤ ስምምነቱ በሁለቱም ወገኖች ላይ የጣለው ግዴታ እንደነበርም ገልጸዋል፡፡ የፌዴራሉ መንግስት የሽብርተኝነት ፍረጃውን እንዲያነሳ ሲገደድ ህወሓት የአገሪቱን ህግ ለማክበር ግዴታ ገብቷል ነው ያሉት፡፡ ህወሓት የፌዴራል ተቋማት ህግን ለማክበር ግዴታ ሲገባ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህግንም ማክበር ነበረበት ብለዋል፡፡ “በዚያው በህጉ መሰረት ህወሓት የሁሉንም ፌዴራል መንግስት ተቋማት ህግ ማክበር ነበረበት” ያሉት የህግ ባለሙያው ህወሓት ከዚያ በማፈንገጥ “ምርጫ ቦርድ ጠቅላላ ጉባኤውን በባለሙያዎቹ ለመታዘብ 21 ቀናት ስጠኝ ብሎት እየጠየቀው” ያንን በመጣስ ጉባኤ አድርጓልም ነው ያሉት፡፡ ይህ ደግሞ መሰረታዊ የምርጫ እና ፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ ህጉን (1162) የሚጥስ ነው ሲሉም አስተያየታቸውን አክለዋል፡፡  
ከጉባኤው የሚጠበቀው ምንም ህጋዊ ይሁኝታ እንደማይጠበቅ ያነሱት የህግ ባለሙያው አቶ አንዱኣለም፤ “የጠቅላላ ጉባኤው ውሳኔ ወንበር እና አዳራሽ ከማሞቅ ያለፈ ፋይዳ አይኖረውም በማለት” ስለሚጠበቀው ጉዳይም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡


 ሥዩም ጌቱ
ልደት አበበ
ኂሩት መለሰ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW