1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ፖለቲካእስያ

የህዝባዊ ቻይና መሪ በሞስኮ

ሰኞ፣ መጋቢት 11 2015

ዢ ጂንፒንግ ለሦስት ቀናት ጉብኝት ዛሬ ጠዋት ሞስኮ ገቡ። የሩስያ የመንግሥት የዜና ወኪል «ሪያ ኖቮስቲ» ዢ ጂንፒንግን የያዘዉ አዉሮፕላን ሞስኮ ቭኑኮቫ ዓለም አቀፍ አዉሮፕላን ማረፍያ መድረሱን የሚያሳይ ፎቶግራፍ አሰራጭቷል። የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዢ ጂንፒንግ ወደ የሩስያ ጉዞን "የሰላም ጉብኝት" በማለት ገልጾታል።

Russland Präsident Xi und Putin
ምስል Sergei Karpukhin/Sputnik/REUTERS

የህዝባዊት ቻይና መሪ ዢ ጂንፒንግ ለሦስት ቀናት ጉብኝት ዛሬ ጠዋት ሞስኮ ገቡ። የሩስያ የመንግሥት የዜና ወኪል «ሪያ ኖቮስቲ» ዢ ጂንፒንግን የያዘዉ አዉሮፕላን ሞስኮ ቭኑኮቫ ዓለም አቀፍ አዉሮፕላን ማረፍያ መድረሱን የሚያሳይ ፎቶግራፍ አሰራጭቷል። የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዢ ጂንፒንግ ወደ የሩስያ ጉዞን "የሰላም ጉብኝት" በማለት ገልጾታል። ዢ ጂንፒንግ  እና የሩሲያዉ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በሁለት ሃገራት ግንኙነቶች እና ዋና ዋና ዓለም አቀፋዊ እና አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል። ከአራት ዓመት ገደማ በኋላ የህዝባዊት ቻይና መሪ ወደ ሞስኮ ሲመጡ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ቻይና እስካሁን የሩስያ በዩክሬን ላይ እያካሄደችዉ ስላችዉ የጦር ወረራ ገለልተኛ ሆና ራሷን ለማቅረብ ጥረት እያደረገች ነዉ። የህዝባዊት ቻይና መሪ ዢ ጂንፒንግ  ሞስኮ ከመድረሳቸዉ በፊት የሩሲያዉ ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን ቻይና የዩክሬንን ጦርነት በማስቆም ረገድ "ገንቢ ሚና" ለመጫወት ፈቃደኛ መሆናቸውን ማድነቃቸዉ ተዘግቧል። (ሬንሚን ሪባኦ) የተባለ የቻይና ጋዜጣ ባወጣው ጽሑፍ ፑቲን "ሩሲያ የዩክሬንን ቀውስ በፖለቲካዊ እና ዲፕሎማስያዊ ዘዴዎች ለመፍታት ዝግጁ ናት" በማለት ጽፈዋል ሲል አስነብቧል። 

አዜብ ታደሰ 

እሸቴ በቀለ 

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW