1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የህዝብ አስተያየት፦ በዋጋ ንረት፣ በትግራይ እና ኤርትራ ጉዳይዮች ላይ

ዓርብ፣ ሰኔ 27 2017

በሰሜን ኢትዮጵያ በተቀሰቀሱ ግጭቶች በተፈጠረው አለመረጋጋት በአከባቢያቸው ህይወታቸውን መምራት ያልቻሉና በአዲስ አበባ ጎዳና ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሚታዩ ዜጎች ቁጥር ቀላል አይደለም፡፡ እነዚህ ዜጎች የዋጋ ንረትን መቋቋም ተስኗቸው ለልመና ጎዳና መውጣታቸውን ይናገራሉ፡፡ ቋሚ የመንግስት ሠራተኞችም ኑሮ እንዳጎበጣቸውበምሬት ያነሳሉ፡፡

አዲስ አበባ መገናኛ እግረኞች መንገድ ሲያቋርጡ
አዲስ አበባ መገናኛ እግረኞች መንገድ ሲያቋርጡምስል፦ Solomon Muchie/DW

የህዝብ አስተያየት፦ በዋጋ ንረት፣ በትግራይ እና ኤርትራ ጉዳይዮች ላይ

This browser does not support the audio element.

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ትናንት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው ለምክር ቤቱ አባላት ከሰጡዋቸው ማብራሪያዎች በትግራይ ክልል የፀጥታ ሁኔታ እና ከጎረቤት ኤርትራ ጋር ኢትዮጵያ ስላላት ወቅታዊ ግንኙነት የሰጡት አስተያየት ትኩረት ስቧል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትግራይ ክልል ግጭት እንዳይነሳ አስቀድሞ እንዲሰራ ጥሪ ባቀረቡበት አስተያየታቸው ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷ እንዲጸና የባህር በር ማግኘት አለባትም ነው ያሉት፡፡ ለግብጽ እና ሌሎች የናይል ተፋሰስ አገራት ያቀረቡት የታላቁ ህዳሴ ግድብን አብሮ የማስመረቅ ጥሪም ትኩረት ስቧል፡፡
ዶይቼ ቬለ በነዚህና በብዙሃን ላይ የከበደውየኑሮ ውድነት እና የሚሰጡ የእድገት ተስፋዎችን በተመለከተ በኢትዮጵያ በተለያዩ አቅጣጫዎች በሚሰጡ አስተያየቶች ላይ የህዝብ አስተያየት አሰባስቧል፡፡

በሰሜን ኢትዮጵያ በተለያዩ ወቅቶች በተቀሰቀሱ ግጭቶች በተፈጠረው አለመረጋጋት በአከባቢያቸው ህይወታቸውን መምራት ያልቻሉና በአዲስ አበባ ጎዳና ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሚታዩ ዜጎች ቁጥር ቀላል አይደለም፡፡ እነዚህ ነዋሪዎች በአከባቢያቸው ግጭቱን ተከትሎ የተፈጠረውን የዋጋ ንረትና የኑሮ መክበድ መቋቋም ተስኗቸው ለልመና ጎዳና መውጣታቸውን ሳይሸሽጉ ይናገራሉ፡፡

አዲስ አበባ ከተማምስል፦ Solomon Muchie/DW


በኢትዮጵያ በተለይም በቋሚ የመንግስት ስራ ደመወዝ የሚተዳደሩ ኑሮ እንዳጎበጣቸው ተደጋግመው በምሬት ያነሳሉ፡፡
ትናንት በኢትዮጵያ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የምክር ቤቱ አባላትም ይህንኑን የህዝብ እሮሮ ሲያስተጋቡ የተደመጡ ሲሆን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድም ጥያቄውና እልባቱ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡበት ስወተውቱም ነበር፡፡
አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡ የተለያዩ የማህበረሰብ አካላት መሬት ላይ ያለው የኑሮ መናርን በመግለጽ ለመፍትሄው አቤት ብለዋል፡፡
የመንግስት ሰራተኞች በፊናቸው ከደመወዝም በላይ መንግስት በጥቅማጥቅሞች ልደርስላቸው ካልቻለ በዚህ መልኩ ኑሮን መግፋት በእጅጉ እንደከበደባቸው እያነሱ ነው፡፡
ስዩም ጌቱ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ
 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ
ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW