የህዳሴ ግድብ ድርድርና የኢትዮጵያ ፍላጎት
ሰኞ፣ ሰኔ 6 2014![Äthiopien Guba | Grand-Ethiopian-Renaissance-Talsperre](https://static.dw.com/image/60846492_800.webp)
ማስታወቂያ
ኢትዮጵያን ጨምሮ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ውሃ አያያዝ ላይ የሚወዛገቡት ሶስቱ አገራት ወደ አቋረጡት የሶስትዮሽ ድርድር ሊመለሱ እንደሚችሉ መረጃዎች እየተሰማ ነው፡፡በኢትዮጵያ በኩል የተሰጠ የተረጋገጠ መረጃ ባይኖርም የሶስትዮሽ ድርድሩ ወደ የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች ሊወሰድ እንደሚችልም የዘገቡ አሉ፡፡በኢትዮጵያ መንግስት በኩል ቢያንስ እስካሁን በይፋ የሚታወቀው የኢትዮጵያ አቋም ድርድሩ በአፍሪካ ህብረት ማዕቀፍ እንደሚቀጥል መሆኑ ነው፡፡ የአዲስ አበባ ዘጋቢያችን ሥዩም ጌቱ በግድቡ ዙሪያ ስለሚነሱ ሀሳቦች የውሃ ሃብት አስተዳደር ባለሙያን ጠይቆ ዘገባ አሰናድቷል፡፡ከሚመለከታቸው የመንግስት ባለስልጣናት መረጃ ለማግኘት ያደረገው ጥረት ግን አልተሳካም።
ስዩም ጌቱ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ