የህዳሴ ግድብ ግንባታ 3ኛ ዓመት
እሑድ፣ መጋቢት 14 2006ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ የሕዝቧን ፍላጎት እና ኢንዱስትሪዎችን የማስፋፋት ጥረቷን ለማርካት አሁን ያሏት ግድቦች በቂ እንዳልሆኑ በመገንዘብ በዓባይ ወንዝ ላይ 6,000 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ይኖረዋል የሚባለውን የህዳሴ ግድብ ግንባታን በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጀምራለች። እአአ በ2015 ዓም በተወሰነ ደረጃ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ይጀምራል የሚባለው እና እአአ በ2017 ዓም እንደሚጠናቀቅ የተነገረለት የግድቡ ግንባታ ከተጀመረ አሁን ሦስተኛ ዓመት የሆነበትን ምክንያት መነሻ በማድረግ የህዳሴ ግድብ ግንባታ እና ሂደቱ ምን ደረጃ ላይ ይገኛል? ተወያይተንበታል።
አርያም ተክሌ
ልደት አበበ