ትኩረት በአፍሪቃ 12.08.2023
ቅዳሜ፣ ነሐሴ 6 2015
በወርቅ እና በአልማዝ በበለፀገችው አፍሪቃዊት ሀገር ፤ማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ በቅርቡ ሁከትና ብጥብጥን የሚያነግስ ሕገ መንግሥታዊ ለውጥ እንዲመጣ ዜጎቿ ድምፅ ሰጥተዋል። ይህ አዲስ ህዝበ ውሳኔ እና ለህገ-መንግስታዊ ለውጥ ፕሬዝዳንት ፋውስቲን-አርቼንጅ ቱአዴራ ለሶስተኛ ጊዜ የስልጣን ዘመናቸውን እንዲያራዝሙ የሚያደርግ በመሆኑ በሀገሪቱ ውዝግብ አስከትሏል።ፕሬዚዳንቱ ግን ደስተኛ ናቸው።
«የዜግነት ግዴታን የመወጣት ስሜት ነው። የተሳካልኝ ሆኖ ይሰማኛል። ከማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ የመጡ ወገኖቼ ድምጽ ለመስጠት እንደመጡ ሁሉ የዜግነት ግዴታዬን ተወጥቻለሁ። ኩራት ይሰማኛል. ምክንያቱም የማዕከላዊ አፍሪካ ሕዝብ ጥያቄ ነበር።»
አዲሱ ህግ አሁን ያለውን የሁለት ጊዜ ገደብ በመሻር የፕሬዚዳንቱን ስልጣን ከአምስት ወደ ሰባት አመታት ያራዝመዋል።ባለሁለት ዜግነት ያላቸው ፖለቲከኞች ሌላውን ካልተው በስተቀር ለፕሬዚዳንትነት እንዳይወዳደሩም ይከለክላል።
95% መራጮች ደግፈውታል የተባለው ይህ ህዝበ ውሳኔ ፤ተቺዎች እንደሚሉት የምርጫው ሂደት ግልፅነት የጎደለው እና በቂ ምክክር ያልተደረገበት ነው።በምርጫው የተገኘው ውጤትም 10 በመቶ ዝቅተኛ ነበር።የመአከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ ምርጫ
በጎርጎሪያኑ ሀምሌ 30 ቀን 2023 የተካሄደውን ይህ ህዝበ ውሳኔ፤ ፕሬዝዳንቱ የፈለጉትን ያህል ጊዜ እንዲወዳደሩ የሚፈቅድ ሲሆን፤ተቃዋሚ ፓርቲዎች እና አንዳንድ የሲቪል ማህበረሰብ ቡድኖች ፕሬዝደንት ቱዋዴራን እድሜልካቸውን በስልጣን ላይ እንዲቆዩ ለማድረግ የተነደፈ "ህገ መንግስታዊ መፈንቅለ መንግስት" ሲሉ ይተቹታል። የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው ክሬፒን ምቦሊ ንጎምባ፣ ዜጎች በምርጫው እንዳይሳተፉም አስቀድመው ጠይቀው ነበር።
«ህገ ወጥ የሆነውን ሂደት መቀላቀል ለህገ-ወጥ ሂደት ህጋዊነት መስጠት ነው። ያንን ማድረግ የምንችልበት ምንም መንገድ የለም። ሂደቱ በሙሉ ህገወጥ መሆኑን ሰዎች ማስታወስ አለባቸው። በእርግጥ የዚህ ተቋም ፕሬዚዳንት መመሪያዎችን ለማግኘት ወደ ሩሲያ ሄዷል።.የአሁኑ የሕገ መንግሥት ፍርድ ቤት ህጋዊ ፕሬዚዳንትም መመሪያ ለመውሰድ ወደ ሩሲያ ሄዷል። እኛ ግልፅ የምናደርግበት ምንም መንገድ የሌለው የተበላሸ ሂደት ነው። ቱአዲር ለማሳካት እየሞከሩ ያለት አምባገነን ስርዓት ለመመስረት ነው።»
ፕረዚደንት ፋውስቲን-አርሴንጅ ቱዋዴራ በሩሲያ የዋግነር ቅጥረኞች ይደገፋሉ ከህዝበ ውሳኔው በፊት ተጨማሪ ተዋጊዎች ደርሰዋል ሲሉም ይከሷቸዋል።
ኢቫሪስቴ ንጋማና-የህዝበ ውሳኔው ብሔራዊ ዘመቻ ዳይሬክተር ግን ክሱን አይቀበሉትም።እንዲያውም ትችቱ ህዝብን መናቅ ነው ይላሉ።
« የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ህዝቦች በሙሉ በሩሲያውያን ተታለዋል ትላለህ... አይሆንም! ለመካከለኛው አፍሪካ ህዝብ ትንሽ ክብር እንዲኖራችሁ በትህትና እጠይቃችኋለሁ። ከህዝብ በላይ የሆነ ተቋም የለም። በሕዝብ የተጠየቀውን በጽሑፍ መደበኛ ከማድረግ ውጪ ሌላ ዓላማ የለንም።»
የዋግነር ሃይሎች አሁንም ሰፊ የሀገሪቱን አካባቢዎች የሚቆጣጠሩትን አማፂ ቡድኖችን ለመዋጋት ፕሬዝዳንት ቱዋዴራን ሲደግፉ የጦር ወንጀል ፈጽመዋል ተብለውም ይከሰሳሉ።በማዕድን እና በእንጨት ኢንዱስትሪዎች ላይም ድርሻቸው ከፍተኛ ነው ይባላል።
ወደብ አልባዋ ማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ ከጠቅላላው ህዝብ ሲሶውን ከመኖሪያ ቤቱ ባፈናቀለ የዕርስ በዕርስ ጦርነት ውስጥ የምትገኝ እና 60 በመቶ ህዝቧ በድህነት የሚኖርባት ሀገር ነች።
ሀገሪቱ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ሕገ መንግስታቸውን ከለወጡት ቡሩንዲ፣ኡጋንዳ እና ሩዋንዳ ከመሳሰሉ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ጋር ተቀላቅላለች።የብሩንዲ የማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክና የማሊ ቀውስ
ፕሬዝዳንቱ "የህዝቡን ፍላጎት" እየተከተልኩ ነው ይላሉ።ነገር ግን ጉዳዩ በሀገሪቱ ዲሞክራሲ ላይ የሚነሱ ጥያቄዎች ፣እንዲሁም ሩሲያ በሌላ የአፍሪቃ ሀገር ጉዳይ የተጫወተችው ሚና መልስ አላገኘም።
ፀሀይ ጫኔ
እሸቴ በቀለ