የለንደኑ ኦሎምፒክና የፀጥታ ጥበቃ
ረቡዕ፣ ሐምሌ 18 2004ማስታወቂያ
ከነገ በስተያ አርብ የሚጀመረው የለንደኑ የኦሎምፒክ ውድድር በስፖርተኞችና በመላው ስፖርት አፍቃሪዎች ዘንድ በጉጉት እየተጠበቀ ነው ። በአሁኑ ጊዜም የሁሉም ዓይን ወደ ለንደን አትኩሯል ። የፀጥታ ቁጥጥሩም ተጠናክሮ ቀጥሏል ። ለኦሎምፒክ ጨዋታ ፀጥታ ጥበቃ ከ 18 ሺህ በላይ ወታደሮች ተዘጋጅተዋል ። አስፈላጊዎቹ የፀጥታ መቆጣጠሪያ መሳሪያዎችም በየቦታው ተተክለዋል ። የብሪታኒያ ፖሊስ እንደሚለው የፀጥታ ጥበቃ ሠራተኞች ለማናቸውም አስጊ ለሚባሉ የአሸባሪዎች እንቅስቃሴዎች በተጠንቀቅ ላይ ናቸው ። በመስኩ የተሰማሩ አስተያየት ሰጭዎች እንደሚሉት ደግሞ ብሪታኒያ በታሪኳ እንደ ዘንድሮው ከባድ ፈተና ውስጥ አልገባችም ። ከለንደን ሽቴፋን ቢርድ ያላከውን ዘገባ ይልማ ኃይለ ሚካኤል አጠናክሮታል .
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ሂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ