የለንደኑ የእሳት አደጋ
ዓርብ፣ ሰኔ 9 2009ማስታወቂያ
በዚህ ሰሞን ምዕራብ ለንደን ውስጥ በሚገኝ ባለ 24 ፎቅ የመኖርያ ህንፃ ላይ በደረሰው የእሳት አደጋ የሞቱት ቁጥር ወደ 30 ከፍ ማለቱ ዛሬ ተነገረ። ከሟቾቹ መካከል ህጻናትን ጨምሮ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ይገኙበታል። የእሳት አደጋው የተነሳው ከአንድ ኢትዮጵያዊ መኖሪያ ቤት መሆኑን ዴይሊሜይል ዘግቧል። የመንግሥት ምንጮች ግን ይህን አላረጋገጡም። በአደጋው የሞቱት ቁጥር ከ150 በላይ ሊሆን ይችላል የሚሉ ግምቶች ይሰማሉ። የለንደንዋ ዘጋቢያችን ሀና ደምሴ ዝርዝሩን አዘጋጅታለች።
ሀና ደምሴ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ